መዝሙር 116:1-19

  • የምስጋና መዝሙር

    • “ለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ?” (12)

    • “የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ” (13)

    • “ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ” (14, 18)

    • የአገልጋዮቹ ሞት በይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር ነው (15)

116  ይሖዋ ድምፄን፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ።*+   ጆሮውን ወደ እኔ ያዘነብላልና፣*+በሕይወት እስካለሁ ድረስ* እሱን እጣራለሁ።   የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤መቃብር ያዘኝ።*+ በጭንቀትና በሐዘን ተዋጥኩ።+   እኔ ግን የይሖዋን ስም ጠራሁ፦+ “ይሖዋ ሆይ፣ ታደገኝ!”*   ይሖዋ ሩኅሩኅና* ጻድቅ ነው፤+አምላካችን መሐሪ ነው።+   ይሖዋ ተሞክሮ የሌላቸውን ይጠብቃል።+ ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ እሱ ግን አዳነኝ።   ነፍሴ* ዳግመኛ እረፍት ታግኝ፤ይሖዋ ደግነት አሳይቶኛልና።   እኔን* ከሞት፣ ዓይኔን ከእንባ፣እግሬንም ከእንቅፋት ታድገሃል።+   በሕያዋን ምድር በይሖዋ ፊት እሄዳለሁ። 10  አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ፤+እጅግ ተጎሳቁዬ ነበር። 11  በጣም ደንግጬ “ሰው ሁሉ ውሸታም ነው”+ አልኩ። 12  ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ? 13  የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ፤የይሖዋንም ስም እጠራለሁ። 14  በሕዝቡ ሁሉ ፊትስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ።+ 15  የታማኝ አገልጋዮቹ ሞትበይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር* ነው።+ 16  ይሖዋ ሆይ፣እኔ አገልጋይህ ስለሆንኩ እለምንሃለሁ። እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ አገልጋይህ ነኝ። አንተ ከእስራቴ ነፃ አውጥተኸኛል።+ 17  ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤+የይሖዋን ስም እጠራለሁ። 18  በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ፤+ 19  በይሖዋ ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+በኢየሩሳሌም መካከል ስእለቴን አቀርባለሁ። ያህን አወድሱ!*+

የግርጌ ማስታወሻ

“ይሖዋ ስለሚሰማ ውስጤ በፍቅር ይሞላል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ጎንበስ ብሎ ይሰማኛልና።”
ቃል በቃል “በቀኖቼ።”
ቃል በቃል “የሲኦል ጭንቅ አገኘኝ።”
ወይም “ነፍሴን ታደግ።”
ወይም “ቸርና።”
ወይም “ነፍሴን።”
ቃል በቃል “ክቡር።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።