መዝሙር 120:1-7
ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።*
120 በተጨነቅኩ ጊዜ ይሖዋን ተጣራሁ፤+እሱም መለሰልኝ።+
2 ይሖዋ ሆይ፣ ከሐሰተኛ ከንፈር፣ደግሞም ከአታላይ አንደበት ታደገኝ።*
3 አንተ አታላይ አንደበት፣አምላክ ምን ያደርግህ ይሆን? እንዴትስ ይቀጣህ ይሆን?*+
4 ሹል በሆኑ የተዋጊ ፍላጻዎችና+በክትክታ እንጨት ፍም+ ይቀጣሃል።
5 በመሼቅ+ የባዕድ አገር ሰው ሆኜ ስለኖርኩ ወዮልኝ!
በቄዳር+ ድንኳኖች መካከል ኖሬአለሁ።
6 ሰላም ከሚጠሉ ሰዎች ጋርለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ።*+
7 እኔ ለሰላም ቆሜአለሁ፤እነሱ ግን በተናገርኩ ቁጥር ለጦርነት ይነሳሉ።
የግርጌ ማስታወሻ
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”
^ ቃል በቃል “ደግሞስ ምን ይጨምርልህ ይሆን?”
^ ወይም “ነፍሴ ለረጅም ጊዜ ኖራለች።”