መዝሙር 125:1-5

  • ይሖዋ ሕዝቡን ይጠብቃል

    • “ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዳሉ ሁሉ” (2)

    • “በእስራኤል ሰላም ይስፈን” (5)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 125  በይሖዋ የሚታመኑ፣+ፈጽሞ ሳይናወጥ ለዘላለም ጸንቶ እንደሚኖረውእንደ ጽዮን ተራራ ናቸው።+   ተራሮች በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንዳሉ ሁሉ፣+ይሖዋም ከአሁን ጀምሮ ለዘላለምበሕዝቡ ዙሪያ ይሆናል።+   ጻድቃን ትክክል ያልሆነ ነገር መሥራት እንዳይጀምሩ፣*+የክፋት በትር ለጻድቃን በተሰጠ ምድር ላይ አይኖርም።+   ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩ ሰዎች፣ለልበ ቅኖች+ መልካም ነገር አድርግ።+   ወደ ጠማማ መንገዳቸው ዞር የሚሉትን፣ይሖዋ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ያስወግዳቸዋል።+ በእስራኤል ሰላም ይስፈን።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳያዞሩ።”