መዝሙር 129:1-8

  • አጠቁኝ፤ ሊያሸንፉኝ ግን አልቻሉም

    • ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ኀፍረት ይከናነባሉ (5)

ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር። 129  “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር”፤+ እስራኤል እንዲህ ይበል፦   “ከወጣትነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ያጠቁኝ ነበር፤+ሆኖም ሊያሸንፉኝ አልቻሉም።+   አራሾች ጀርባዬን አረሱት፤+ትልማቸውንም አስረዘሙት።”*   ይሖዋ ግን ጻድቅ ነው፤+የክፉዎችን ገመድ በጣጥሷል።+   ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ኀፍረት ይከናነባሉ፤ ተዋርደውም ወደኋላቸው ይመለሳሉ።+   ከመነቀሉ በፊት እንደሚጠወልግ፣በጣሪያ ላይ እንደበቀለ ሣር ይሆናሉ፤   እንዲህ ዓይነቱ ሣር የአጫጁን እጅ፣ነዶ የሚሰበስበውንም ሰው ክንዶች ሊሞላ አይችልም።   በዚያ የሚያልፉ ሰዎች “የይሖዋ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤በይሖዋ ስም እንባርካችኋለን” አይሉም።

የግርጌ ማስታወሻ

ይህ ጠላቶቻቸው የሚፈጽሙባቸውን የጭካኔ ድርጊት ያሳያል።