መዝሙር 132:1-18
ወደ ላይ የመውጣት መዝሙር።
132 ይሖዋ ሆይ፣ ዳዊትን፣የደረሰበትንም መከራ ሁሉ አስታውስ፤+
2 ለይሖዋ እንዴት እንደማለ፣ኃያል ለሆነው ለያዕቆብ አምላክ እንዴት እንደተሳለ አስብ፦+
3 “ወደ ድንኳኔ፣ ወደ ቤቴ አልገባም።+
ወደ መኝታዬ፣ ወደ አልጋዬ አልወጣም፤
4 ዓይኖቼ እንዲያንቀላፉ፣ሽፋሽፍቶቼም እንዲያሸልቡ አልፈቅድም፤
5 ይህም ለይሖዋ ስፍራ፣ኃያል ለሆነው የያዕቆብ አምላክም ያማረ መኖሪያ እስከማገኝ ድረስ ነው።”+
6 እነሆ፣ በኤፍራታ+ ስለ እሷ ሰማን፤በጫካ በተሞላው ምድር አገኘናት።+
7 ወደ መኖሪያው እንግባ፤+በእግሩ ማሳረፊያ ፊት እንስገድ።+
8 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤አንተና የብርታትህ ታቦት፣+ ወደ ማረፊያ ስፍራህ ሂዱ።+
9 ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ታማኝ አገልጋዮችህም እልል ይበሉ።
10 ለአገልጋይህ ለዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ።+
11 ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦
“ከዘሮችህ መካከል አንዱን*በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።+
12 ወንዶች ልጆችህ ቃል ኪዳኔንናየማስተምራቸውን ማሳሰቢያዎች ቢጠብቁ፣+የእነሱም ልጆችለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ።”+
13 ይሖዋ ጽዮንን መርጧታልና፤+የራሱ መኖሪያ እንድትሆን ፈልጓል፤+ እንዲህም ብሏል፦
14 “ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤በእሷ እኖራለሁ፤+ ይህ ምኞቴ ነውና።
15 የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤ድሆቿን እህል አጠግባለሁ።+
16 ካህናቷ መዳንን እንዲለብሱ አደርጋለሁ፤+ታማኝ ሕዝቦቿም እልል ይላሉ።+
17 በዚያ የዳዊትን ብርታት እጨምራለሁ።*
ለቀባሁት አገልጋዬ መብራት አዘጋጅቻለሁ።+
18 ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባለሁ፤በራሱ ላይ ያለው አክሊል* ግን ያብባል።”+