መዝሙር 136:1-26

  • የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል

    • ሰማይንና ምድርን በጥበብ ሠራ (5, 6)

    • ፈርዖን ቀይ ባሕር ውስጥ ሞተ (15)

    • አምላክ የተጨነቁትን ያስታውሳል (23)

    • “ሕይወት ላለው ሁሉ ምግብ ይሰጣል” (25)

136  ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+   ለአማልክት አምላክ+ ምስጋና አቅርቡ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።   ለጌቶች ጌታ ምስጋና አቅርቡ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።   እሱ ብቻ አስደናቂ የሆኑ ታላላቅ ነገሮች ይሠራል፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።+   ሰማያትን በጥበብ ሠራ፤*+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።   ምድርን በውኃዎች ላይ ዘረጋ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።   ታላላቅ ብርሃናትን ሠራ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤   ፀሐይ በቀን እንዲያይል* አደረገ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤   ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲያይሉ* አደረገ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 10  የግብፅን በኩር ቀሰፈ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 11  እስራኤልን ከመካከላቸው አወጣ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ 12  በኃያል እጅና በተዘረጋ ክንድ ይህን አድርጓል፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 13  ቀይ ባሕርን ለሁለት ከፈለ፤*+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 14  እስራኤል በመካከሉ እንዲያልፍ አደረገ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 15  ፈርዖንንና ሠራዊቱን ቀይ ባሕር ውስጥ ወረወረ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 16  ሕዝቡን በምድረ በዳ መራ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 17  ታላላቅ ነገሥታትን መታ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 18  ኃያላን ነገሥታትን ገደለ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ 19  የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን+ ገደለ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ 20  የባሳንንም ንጉሥ ኦግን+ ገደለ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 21  ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሰጠ፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና፤ 22  ለአገልጋዩ ለእስራኤል ርስት አድርጎ አወረሰ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 23  መንፈሳችን ተደቁሶ በነበረበት ጊዜ አስታወሰን፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።+ 24  ከጠላቶቻችን እጅ ይታደገን ነበር፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 25  ሕይወት ላለው* ሁሉ ምግብ ይሰጣል፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። 26  ለሰማያት አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በማስተዋል ሠራ።”
ወይም “እንዲገዛ።”
ወይም “እንዲገዙ።”
ቃል በቃል “በታተነ።”
ቃል በቃል “ለሥጋ።”