መዝሙር 14:1-7

  • የሞኝ ሰው መገለጫ

    • “ይሖዋ የለም” (1)

    • “መልካም የሚሠራ ማንም የለም” (3)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር። 14  ሞኝ* ሰው በልቡ “ይሖዋ የለም” ይላል።+ ሥራቸው ብልሹ ነው፤ ተግባራቸውም አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+   ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት፣ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+   ሁሉም መንገድ ስተዋል፤+ሁሉም ብልሹ ናቸው። መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤አንድ እንኳ የለም።   ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም? ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ። ይሖዋን አይጠሩም።   ይሁንና በታላቅ ሽብር ይዋጣሉ፤+ይሖዋ ከጻድቅ ትውልድ ጋር ነውና።   እናንተ ክፉ አድራጊዎች የችግረኛውን ሰው ዕቅድ ለማጨናገፍ ትሞክራላችሁ፤ይሖዋ ግን መጠጊያው ነው።+   የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+ ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ማመዛዘን የጎደለው።”