መዝሙር 142:1-7
ማስኪል።* ዳዊት ዋሻ ውስጥ በነበረበት ጊዜ+ የዘመረው መዝሙር። ጸሎት።
142 ድምፄን አውጥቼ እርዳታ ለማግኘት ወደ ይሖዋ እጣራለሁ፤+ሞገስ እንዲያሳየኝ ይሖዋን እማጸናለሁ።
2 የሚያሳስበኝን ነገር በፊቱ አፈስሳለሁ፤የውስጤን ጭንቀት በፊቱ እናገራለሁ፤+
3 መንፈሴ* በውስጤ ሲዝል፣ እሱን እማጸናለሁ።
በዚህ ጊዜ ጎዳናዬን ትመለከታለህ።+
በምሄድበት መንገድ ላይበስውር ወጥመድ ዘረጉብኝ።
4 ቀኝ እጄን ተመልከት፤ስለ እኔ ግድ የሚሰጠው* ሰው እንደሌለ እይ።+
ሸሽቼ ማምለጥ የምችልበት ቦታ የለም፤+ስለ እኔ* የሚያስብ ማንም የለም።
5 ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ እጣራለሁ።
ደግሞም “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤+በሕያዋን ምድር ያለኸኝ አንተ ብቻ* ነህ” እላለሁ።
6 መንፈሴ እጅግ ተደቁሷልና፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስማ።
ከእኔ ይልቅ ብርቱ ስለሆኑከሚያሳድዱኝ ሰዎች ታደገኝ።+
7 ስምህን አወድስ ዘንድከእስር ቤት አውጣኝ።*
ደግነት ስለምታሳየኝጻድቃን በዙሪያዬ ይሰብሰቡ።