መዝሙር 144:1-15

  • ድል ለመቀዳጀት የቀረበ ጸሎት

    • “ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?” (3)

    • ‘ጠላቶች ይበተኑ’ (6)

    • የይሖዋ ሕዝብ ደስተኛ ነው (15)

የዳዊት መዝሙር። 144  እጆቼን ለውጊያ፣ጣቶቼንም ለጦርነት የሚያሠለጥነው፣+ዓለቴ የሆነው ይሖዋ+ ይወደስ።   እሱ ታማኝ ፍቅር የሚያሳየኝ አምላኬና ምሽጌ፣አስተማማኝ መጠጊያዬና ታዳጊዬ፣ጋሻዬና መጠለያዬ፣+ሕዝቦችን ከበታቼ የሚያስገዛልኝ አምላኬ ነው።+   ይሖዋ ሆይ፣ ታስተውለው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ቦታ ትሰጠውስ ዘንድ ሟች የሆነው የሰው ልጅ ምንድን ነው?+   ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤+ዘመኑ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።+   ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያትህን ወደ ታች ዝቅ አድርገህ* ውረድ፤+ተራሮችን ዳስሰህ እንዲጨሱ አድርግ።+   መብረቅ ልከህ ጠላትን በትን፤+ፍላጻዎችህን ወርውረህ ግራ አጋባቸው።+   እጆችህን ከላይ ዘርጋ፤ከሚያጥለቀልቅ ውኃ ታደገኝ፤ ደግሞም አድነኝ፤ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ* አስጥለኝ፤+   እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ።*   አምላክ ሆይ፣ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ።+ አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የታጀበ የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ፤ 10  እሱ ነገሥታትን ድል* ያጎናጽፋል፤+አገልጋዩን ዳዊትን ከገዳይ ሰይፍ ይታደጋል።+ 11  ከባዕድ አገር ሰዎች እጅ ታደገኝ፤ አድነኝም፤እነሱ በአፋቸው ውሸት ይናገራሉ፤ደግሞም በውሸት ለመማል ቀኝ እጃቸውን ወደ ላይ ያነሳሉ። 12  ያን ጊዜ ወንዶች ልጆቻችን በፍጥነት እንደሚያድጉ ችግኞች፣ሴቶች ልጆቻችን ደግሞ ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ እንደተቀረጹ የማዕዘን ዓምዶች ይሆናሉ። 13  ጎተራዎቻችን በልዩ ልዩ የእህል ዓይነቶች ጢም ብለው ይሞላሉ፤በመስክ ያሉት መንጎቻችን ተራብተው ሺዎች ደግሞም አሥር ሺዎች ይሆናሉ። 14  የከበዱት ከብቶቻችን ጉዳት አይደርስባቸውም ወይም አይጨነግፉም፤በአደባባዮቻችን ላይ የጭንቅ ዋይታ አይሰማም። 15  ይህ የሚሆንለት ሕዝብ ደስተኛ ነው! አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ ደስተኛ ነው!+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “አጥፈህ።”
ወይም “መዳፍ።”
ቃል በቃል “ቀኝ እጃቸውም የውሸት ቀኝ እጅ ናት።”
ወይም “መዳን።”