መዝሙር 146:1-10
146 ያህን አወድሱ!*+
ሁለንተናዬ* ይሖዋን ያወድስ።+
2 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይሖዋን አወድሳለሁ።
በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።
3 በመኳንንትም* ሆነማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ።+
4 መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+
5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፣+በአምላኩ በይሖዋ ተስፋ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤+
6 እሱ የሰማይ፣ የምድር፣የባሕርና በውስጣቸው ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ነው፤+ደግሞም ለዘላለም ታማኝ ነው፤+
7 ግፍ ለተፈጸመባቸው ፍትሕ ያሰፍናል፤ለተራቡት ምግብ ይሰጣል።+
ይሖዋ እስረኞችን ነፃ ያወጣል።*+
8 ይሖዋ የዓይነ ስውራንን ዓይን ያበራል፤+ይሖዋ ያጎነበሱትን ቀና ያደርጋል፤+ይሖዋ ጻድቃንን ይወዳል።
9 ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን ይጠብቃል፤አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይደግፋል፤+የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያጨናግፋል።*+
10 ይሖዋ ለዘላለም ይነግሣል፤+ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይገዛል።
ያህን አወድሱ!*