መዝሙር 149:1-9

  • አምላክን ለተቀዳጀው ድል በመዝሙር ማወደስ

    • አምላክ በሕዝቡ ደስ ይሰኛል (4)

    • የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች ክብር ይገባቸዋል (9)

149  ያህን አወድሱ!* ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+በታማኝ አገልጋዮች ጉባኤ መካከል አወድሱት።+   እስራኤል በታላቅ ሠሪው+ ሐሴት ያድርግ፤የጽዮን ልጆች በንጉሣቸው ደስ ይበላቸው።   ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፤+በአታሞና በበገና የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት።+   ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛልና።+ እሱ የዋሆችን በማዳን ውበት ያጎናጽፋቸዋል።+   ታማኝ አገልጋዮቹ በክብር ሐሴት ያድርጉ፤በመኝታቸው ላይ ሆነው እልል ይበሉ።+   አንደበታቸው አምላክን የሚያወድስ መዝሙር ይዘምር፤እጃቸውም በሁለቱም በኩል የተሳለ ሰይፍ ይያዝ፤   ይህም በብሔራት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ፣ሕዝቦችንም እንዲቀጡ፣   ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎችም በእግር ብረት እንዲያስሩ፣   ደግሞም በእነሱ ላይ የተላለፈውን በጽሑፍ የሰፈረ ፍርድ እንዲፈጽሙ ነው።+ ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ይህ ክብር ይገባቸዋል። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።