መዝሙር 19:1-14

  • የአምላክ የፍጥረት ሥራና ሕግ ምሥክርነት ይሰጣሉ

    • “ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ” (1)

    • የአምላክ ፍጹም ሕግ ኃይልን ያድሳል (7)

    • ‘ሳላውቅ የሠራኋቸው ኃጢአቶች’ (12)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 19  ሰማያት የአምላክን ክብር ይናገራሉ፤+ጠፈርም የእጆቹን ሥራ ያውጃል።+   በየዕለቱ ንግግራቸው ይሰማል፤በእያንዳንዱም ሌሊት እውቀትን ይገልጣሉ።   ንግግር የለም፤ ቃልም የለም፤ድምፃቸው አይሰማም።   ይሁንና ጩኸታቸው* ወደ መላው ምድር ወጣ፤መልእክታቸውም እስከ ዓለም* ዳርቻዎች ተሰማ።+ እሱ በሰማያት ለፀሐይ ድንኳን ተክሏል፤   ፀሐይም ከጫጉላ ቤት እንደሚወጣ ሙሽራ ነው፤በጎዳናው ላይ እንደሚሮጥ ብርቱ ሰው ደስ ይለዋል።   ከአንደኛው የሰማያት ዳርቻ ይወጣል፤ዞሮም ወደ ሌላኛው ዳርቻ ይሄዳል፤+ከሙቀቱም የሚሰወር አንዳች ነገር የለም።   የይሖዋ ሕግ ፍጹም ነው፤+ ኃይልን ያድሳል።*+ የይሖዋ ማሳሰቢያ አስተማማኝ ነው፤+ ተሞክሮ የሌለውን ጥበበኛ ያደርጋል።+   የይሖዋ መመሪያዎች ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ፤+የይሖዋ ትእዛዝ ንጹሕ ነው፤ ዓይንን ያበራል።+   ይሖዋን መፍራት+ ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል። የይሖዋ ፍርዶች እውነት ናቸው፤ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው።+ 10  ከወርቅ እንዲያውም ብዛት ካለው ምርጥ ወርቅ*የበለጠ የሚወደዱ ናቸው፤+ደግሞም ከማርና ከማር እንጀራ ከሚንጠባጠብ ወለላ ይበልጥ ይጣፍጣሉ።+ 11  ለአገልጋይህ ማስጠንቀቂያ ሆነውለታል፤+እነሱን መጠበቅ ትልቅ ወሮታ አለው።+ 12  የራሱን ስህተት ማን ሊያስተውል ይችላል?+ ሳላውቅ የሠራኋቸውን ኃጢአቶች አትቁጠርብኝ። 13  አገልጋይህንም ከእብሪት ድርጊቶች ጠብቀው፤+እንዲቆጣጠሩኝም አትፍቀድ።+ ያን ጊዜ እንከን የሌለብኝ እሆናለሁ፤+ዓይን ካወጣ ኃጢአትም* ነፃ እሆናለሁ። 14  ዓለቴና+ አዳኜ+ ይሖዋ ሆይ፣ የአፌ ቃልና በልቤ የማሰላስለው ነገርአንተን ደስ የሚያሰኝ ይሁን።+

የግርጌ ማስታወሻ

“መለኪያ ገመዳቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ፍሬያማ እስከሆነው ምድር።”
ወይም “ነፍስን ያድሳል (ይመልሳል)።”
ወይም “ብዛት ካለው የጠራ ወርቅ።”
ወይም “ከብዙ በደልም።”