መዝሙር 20:1-9

  • አምላክ የቀባውን ንጉሥ ያድናል

    • አንዳንዶች በሠረገሎችና በፈረሶች ይታመናሉ፤ ‘እኛ ግን የይሖዋን ስም እንጠራለን’ (7)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። 20  በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ። የያዕቆብ አምላክ ስም ይጠብቅህ።+   ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ፤+ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።+   በስጦታ የምታቀርበውን መባ ሁሉ ያስብልህ፤የሚቃጠል መባህን በሞገስ ዓይን* ይቀበልህ። (ሴላ)   የልብህን ፍላጎት ያሟላልህ፤+ዕቅድህንም* ሁሉ ያሳካልህ።   በማዳን ሥራህ በደስታ እልል እንላለን፤+በአምላካችን ስም ዓርማችንን ወደ ላይ ከፍ እናደርጋለን።+ ይሖዋ የለመንከውን ሁሉ ይፈጽምልህ።   ይሖዋ የቀባውን እንደሚያድን አሁን አወቅኩ።+ በቀኝ እጁ በሚያከናውነው ታላቅ የማዳን ሥራ፣*+ቅዱስ ከሆኑት ሰማያቱ ይመልስለታል።   አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+   እነሱ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤እኛ ግን ተነስተን ቀጥ ብለን ቆመናል።+   ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡን አድን!+ እርዳታ ለማግኘት በተጣራን ቀን ይመልስልናል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “እንደ ስብ ቆጥሮ።”
ወይም “ምክርህንም።”
ወይም “በሚቀዳጀው ታላቅ ድል።”