መዝሙር 27:1-14

  • ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው

    • የአምላክን ቤተ መቅደስ በአድናቆት መመልከት (4)

    • ‘አባቴና እናቴ ቢተዉኝ ይሖዋ ይቀበለኛል’ (10)

    • “ይሖዋን ተስፋ አድርግ” (14)

የዳዊት መዝሙር። 27  ይሖዋ ብርሃኔና+ አዳኜ ነው። ማንን እፈራለሁ?+ ይሖዋ የሕይወቴ ተገን ነው።+ ማን ያሸብረኛል?   ክፉዎች ሥጋዬን ለመብላት ባጠቁኝ ጊዜ፣+ተሰናክለው የወደቁት ባላጋራዎቼና ጠላቶቼ ናቸው።   ሠራዊት በዙሪያዬ ቢሰፍርም፣ልቤ በፍርሃት አይዋጥም።+ ጦርነት ቢከፈትብኝም እንኳበልበ ሙሉነት እመላለሳለሁ።   ይሖዋን አንድ ነገር ለመንኩት፤ምኞቴም ይኸው ነው፦በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት እኖር ዘንድ፣+ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት እመለከት ዘንድ፣ቤተ መቅደሱንም በአድናቆት አይ* ዘንድ ነው።+   በመዓት ቀን በመጠለያው ይሸሽገኛል፤+ሚስጥራዊ ቦታ በሆነው ድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛል፤+ከፍ ባለ ዓለት ላይ ያስቀምጠኛል።+   በመሆኑም ራሴ በዙሪያዬ ካሉ ጠላቶቼ በላይ ከፍ ብሏል፤በድንኳኑ ውስጥ በእልልታ መሥዋዕት አቀርባለሁ፤ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።   ይሖዋ ሆይ፣ በምጮኽበት ጊዜ ስማኝ፤+ሞገስ አሳየኝ፤ መልስም ስጠኝ።+   ልቤ በአንተ ቦታ ሆኖ ሲናገር “ፊቴን ፈልጉ” ብሏል። ይሖዋ ሆይ፣ ፊትህን እሻለሁ።+   ፊትህን ከእኔ አትሰውር።+ አገልጋይህን ተቆጥተህ ፊት አትንሳው። አንተ ረዳቴ ነህ፤+አዳኝ አምላኬ ሆይ፣ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም። 10  የገዛ አባቴና እናቴ ቢተዉኝ እንኳ+ይሖዋ ራሱ ይቀበለኛል።+ 11  ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አስተምረኝ፤+ከጠላቶቼ ጥበቃ እንዳገኝ ቀና በሆነ መንገድ ምራኝ። 12  ለጠላቶቼ* አሳልፈህ አትስጠኝ፤+ሐሰተኛ ምሥክሮች በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤+ደግሞም እኔን ለማጥቃት ይዝቱብኛል። 13  በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮምን ይውጠኝ ነበር!*+ 14  ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤+ደፋር ሁን፤ ልብህም ይጽና።+ አዎ፣ ይሖዋን ተስፋ አድርግ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በተመስጦ እመለከት።”
ወይም “ለጠላቶቼ ነፍስ።”
“በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ” ማለትም ሊሆን ይችላል።