መዝሙር 28:1-9
-
የመዝሙራዊው ጸሎት ተሰሚነት አገኘ
-
‘“ይሖዋ ብርታቴና ጋሻዬ ነው” (7)
-
የዳዊት መዝሙር።
28 ዓለቴ ይሖዋ ሆይ፣ ሁልጊዜ ወደ አንተ እጣራለሁ፤+አንተም ጆሮ አትንፈገኝ።
ዝም ካልከኝ፣ወደ ጉድጓድ* እንደሚወርዱ ሰዎች እሆናለሁ።+
2 ወደ መቅደስህ ውስጠኛ ክፍል እጆቼን አንስቼ፣እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ በምጮኽበት ጊዜ ልመናዬን ስማ።+
3 ከክፉዎችና መጥፎ ነገር ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ጎትተህ አትውሰደኝ፤+እነሱ በልባቸው ክፋት እያለ ከባልንጀሮቻቸው ጋር የሰላም ቃል የሚያወሩ ናቸው።+
4 ለሠሩት ሥራ፣እንደ ክፉ ልማዳቸው ክፈላቸው።+
ለእጃቸው ሥራ መልሰህ ክፈላቸው፤እንዳደረጉትም መልስላቸው።+
5 ይሖዋ ላከናወናቸው ነገሮች፣ለእጆቹም ሥራ ትኩረት አይሰጡምና።+
እሱ ያፈርሳቸዋል፤ ደግሞም አይገነባቸውም።
6 እርዳታ ለማግኘት ያቀረብኩትን ልመና ስለሰማይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።
7 ይሖዋ ብርታቴና+ ጋሻዬ ነው፤+ልቤ በእሱ ይተማመናል።+
ከእሱ እርዳታ ስላገኘሁ ልቤ ሐሴት ያደርጋል፤በመዝሙሬም አወድሰዋለሁ።
8 ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ነው፤ለቀባው ታላቅ መዳን የሚያስገኝ መሸሸጊያ ነው።+
9 ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ።+
ለዘላለም እረኛ ሁናቸው፤ በክንድህም ተሸከማቸው።+
የግርጌ ማስታወሻ
^ ወይም “መቃብር።”