መዝሙር 29:1-11

  • “የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው”

    • ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ ይሖዋን አምልኩ (2)

    • “ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ” (3)

    • “ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል” (11)

የዳዊት ማህሌት። 29  እናንተ የኃያላን ልጆች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+   ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ። ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።*   የይሖዋ ድምፅ ከውኃዎች በላይ ተሰማ፤ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ።+ ይሖዋ ከብዙ ውኃዎች በላይ ነው።+   የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው፤+የይሖዋ ድምፅ ክብራማ ነው።   የይሖዋ ድምፅ አርዘ ሊባኖስን ይሰብራል፤አዎ፣ ይሖዋ አርዘ ሊባኖስን ይሰባብራል።+   ሊባኖስን* እንደ ጥጃ፣ሲሪዮንንም+ እንደ ዱር በሬ እንቦሳ እንዲዘሉ ያደርጋል።   የይሖዋ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል፤+   የይሖዋ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤+ይሖዋ የቃዴስን+ ምድረ በዳ ያናውጣል።   የይሖዋ ድምፅ ርኤሞች* እንዲርበተበቱና እንዲወልዱ ያደርጋል፤ደኖችንም ያራቁታል።+ በቤተ መቅደሱም ውስጥ ያሉ ሁሉ “ክብር ለአምላክ!” ይላሉ። 10  ይሖዋ ከሚያጥለቀልቁት ውኃዎች*+ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ በዙፋን ላይ ይቀመጣል።+ 11  ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል።+ ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል።+

የግርጌ ማስታወሻ

“ከቅድስናው ግርማ የተነሳ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ይሖዋን አምልኩ።”
የሊባኖስን ሰንሰለታማ ተራሮች የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቅርንጫፍ የሚመስሉ ቀንዶች ያሉት አጥቢ እንስሳ፤ ከአጋዘን ጋር ይመሳሰላል።
ወይም “በሰማይ ካለው ውቅያኖስ።”