መዝሙር 31:1-24
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
31 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ።+
ፈጽሞ አልፈር።+
ከጽድቅህ የተነሳ ታደገኝ።+
2 ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል።*
ፈጥነህ ታደገኝ።+
እኔን ለማዳን በተራራ ላይ ያለ ምሽግ፣የተመሸገ ስፍራም ሁንልኝ።+
3 አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ነህና፤+ለስምህ ስትል+ ትመራኛለህ፤ የምሄድበትንም መንገድ ታሳየኛለህ።+
4 አንተ መሸሸጊያዬ ስለሆንክ፣+እነሱ በስውር ከዘረጉብኝ ወጥመድ ታስጥለኛለህ።+
5 መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ።+
የእውነት* አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣+ ዋጅተኸኛል።
6 የማይረቡና ከንቱ የሆኑ ጣዖቶችን የሚያመልኩ ሰዎችን እጠላለሁ፤እኔ ግን በይሖዋ እታመናለሁ።
7 በታማኝ ፍቅርህ እጅግ ሐሴት አደርጋለሁ፤ጉስቁልናዬን አይተሃልና፤+በጭንቀት መዋጤን* ታውቃለህ።
8 ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ይልቁንም ደህንነት በማገኝበት ስፍራ አቆምከኝ።*
9 ይሖዋ ሆይ፣ በጭንቀት ስለተዋጥኩ ሞገስ አሳየኝ።
መከራ ዓይኔንም ሆነ መላ ሰውነቴን አድክሞታል።*+
10 ሕይወቴ በሐዘን፣ዕድሜዬም በመቃተት አልቋል።+
ከፈጸምኩት ኃጢአት የተነሳ ጉልበቴ ተሟጠጠ፤አጥንቶቼ ደከሙ።+
11 ባላጋራዎቼ ሁሉ፣በተለይ ደግሞ ጎረቤቶቼ ተሳለቁብኝ።+
የሚያውቁኝ ሰዎችም እጅግ ፈሩኝ፤በአደባባይ ሲያዩኝ ከእኔ ይሸሻሉ።+
12 የሞትኩ ያህል ከልባቸው ወጣሁ፤* ደግሞም ተረሳሁ፤እንደተሰበረ ማሰሮ ነኝ።
13 ብዙ መጥፎ ወሬ ሰምቻለሁ፤ሽብር ከቦኛል።+
ግንባር ፈጥረው በእኔ ላይ በተነሱ ጊዜሕይወቴን* ለማጥፋት ያሴራሉ።+
14 ይሖዋ ሆይ፣ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።+
“አንተ አምላኬ ነህ” እላለሁ።+
15 የሕይወት ዘመኔ በእጅህ ነው።
ከጠላቶቼና ከሚያሳድዱኝ እጅ ታደገኝ።+
16 ፊትህ በአገልጋይህ ላይ እንዲበራ አድርግ።+
በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ።
17 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በጠራሁ ጊዜ አልፈር።+
ክፉዎች ግን ይፈሩ፤+በመቃብር* ውስጥ ዝም ይበሉ።+
18 በትዕቢትና በንቀት በጻድቁ ላይ በእብሪት የሚናገሩሐሰተኛ ከንፈሮች ዱዳ ይሁኑ።+
19 ጥሩነትህ ምንኛ ብዙ ነው!+
አንተን ለሚፈሩ ጠብቀህ አቆይተኸዋል፤+እንዲሁም አንተን መጠጊያ ለሚያደርጉ ስትል በሰዎች ሁሉ ፊት አሳይተኸዋል።+
20 አንተ ባለህበት ሚስጥራዊ ቦታ፣ከሰዎች ሴራ ትሸሽጋቸዋለህ፤+በመጠለያህ ውስጥከክፉ ጥቃት* ትሰውራቸዋለህ።+
21 በተከበበ ከተማ ውስጥ+ ታማኝ ፍቅሩን በአስደናቂ ሁኔታ ስላሳየኝ+ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።
22 እኔ በድንጋጤ ተውጬ
“ከፊትህ መጥፋቴ ነው” አልኩ።+
አንተ ግን እርዳታ ለማግኘት በጮኽኩ ጊዜ ልመናዬን ሰማህ።+
23 እናንተ ለእሱ ታማኝ የሆናችሁ ሁሉ፣ ይሖዋን ውደዱ!+
ይሖዋ ታማኞችን ይጠብቃል፤+ትዕቢተኛ የሆነን ሰው ግን ክፉኛ ይቀጣል።+
24 እናንተ ይሖዋን የምትጠባበቁ ሁሉ፣+ደፋር ሁኑ፤ ልባችሁም ይጽና።+