መዝሙር 32:1-11

  • ይቅር የተባሉ ደስተኞች ናቸው

    • “ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ” (5)

    • አምላክ ጥልቅ ማስተዋል ይሰጥሃል (8)

የዳዊት መዝሙር። ማስኪል።* 32  በደሉ ይቅር የተባለለት፣ ኃጢአቱ የተሸፈነለት* ሰው+ ደስተኛ ነው።   ይሖዋ በጥፋተኝነት የማይጠይቀው፣በመንፈሱ ሽንገላ የሌለበት ሰው ደስተኛ ነው።+   ዝም ባልኩ ጊዜ፣ ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሳ አጥንቶቼ መነመኑ።+   ቀንና ሌሊት እጅህ* በእኔ ላይ ከብዳለችና።+ በበጋ ንዳድ እንደሚተን ውኃ ኃይሌ ተነነ።* (ሴላ)   በመጨረሻ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ስህተቴን አልሸፋፈንኩም።+ “የፈጸምኳቸውን በደሎች ለይሖዋ እናዘዛለሁ” አልኩ።+ አንተም ስህተቴንና ኃጢአቴን ይቅር አልክ።+ (ሴላ)   ታማኝ የሆነ ሁሉአንተ በምትገኝበት ጊዜ ወደ አንተ የሚጸልየው ለዚህ ነው።+ በዚህ ጊዜ ኃይለኛ ጎርፍ እንኳ አይነካውም።   አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ከጭንቀት ትሰውረኛለህ።+ በድል* እልልታ ትከበኛለህ።+ (ሴላ)   አንተ እንዲህ ብለሃል፦ “ጥልቅ ማስተዋል እሰጥሃለሁ፤ ልትሄድበት የሚገባውንም መንገድ አስተምርሃለሁ።+ ዓይኔን በአንተ ላይ አድርጌ እመክርሃለሁ።+   በልጓም ወይም በልባብ ካልተገራ በስተቀር አልገዛም ብሎወደ እናንተ እንደማይቀርብ፣ማስተዋል እንደሌለው ፈረስ ወይም በቅሎ አትሁኑ።”+ 10  የክፉ ሰው ሥቃይ ብዙ ነው፤በይሖዋ የሚታመን ሰው ግን ታማኝ ፍቅሩ ይከበዋል።+ 11  ጻድቃን ሆይ፣ በይሖዋ ደስ ይበላችሁ፤ ሐሴትም አድርጉ፤ልበ ቀና የሆናችሁ ሁሉ፣ እልል በሉ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “የተተወለት።”
ወይም “ቁጣህ።”
ወይም “የሕይወቴ እርጥበት ተለወጠ።”
ቃል በቃል “በመዳን።”