መዝሙር 33:1-22

  • ለፈጣሪ የቀረበ ውዳሴ

    • “አዲስ መዝሙር ዘምሩለት” (3)

    • ይሖዋ በቃሉና በመንፈሱ የፈጠራቸው ነገ (6)

    • የይሖዋ ሕዝብ ደስተኛ ነው (12)

    • የይሖዋ ዓይኖች በትኩረት ይመለከታሉ (18)

33  እናንተ ጻድቃን ሆይ፣ ይሖዋ ባደረጋቸው ነገሮች የተነሳ እልል በሉ።+ ቅኖች እሱን ማወደሳቸው የተገባ ነው።   ይሖዋን በበገና አመስግኑት፤አሥር አውታር ባለው መሣሪያ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩለት።   አዲስ መዝሙር ዘምሩለት፤+በባለ አውታር መሣሪያ ጥሩ አድርጋችሁ ተጫወቱ፤ እልልም በሉ።   የይሖዋ ቃል ትክክል ነውና፤+ሥራውም ሁሉ እምነት የሚጣልበት ነው።   ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል።+ ምድር በይሖዋ ታማኝ ፍቅር ተሞልታለች።+   ሰማያት በይሖዋ ቃል፣በውስጣቸው ያሉትም ሁሉ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ* ተሠሩ።+   የባሕርን ውኃዎች እንደ ግድብ ያከማቻል፤+የሚናወጠውንም ውኃ በማከማቻ ቦታ ይሰበስባል።   መላዋ ምድር ይሖዋን ትፍራ።+ የምድር ነዋሪዎች እሱን ይፍሩ።*   እሱ ተናግሯልና፣ ሆኗል፤+እሱ አዟል፤ ደግሞም ተፈጽሟል።+ 10  ይሖዋ የብሔራትን ሴራ* አክሽፏል፤+የሕዝቦችን ዕቅድ* አጨናግፏል።+ 11  ይሁንና የይሖዋ ውሳኔዎች ለዘላለም ይጸናሉ፤*+የልቡ ሐሳብ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል። 12  ይሖዋ አምላኩ የሆነ ብሔር፣የራሱ ንብረት አድርጎ የመረጠው ሕዝብ ደስተኛ ነው።+ 13  ይሖዋ ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤የሰው ልጆችን ሁሉ ያያል።+ 14  ከመኖሪያ ቦታው ሆኖበምድር የሚኖሩትን በትኩረት ይመለከታል። 15  የሁሉንም ልብ የሚሠራው እሱ ነው፤ሥራቸውን ሁሉ ይመረምራል።+ 16  በሠራዊት ብዛት የዳነ ንጉሥ የለም፤+ኃያል ሰው በታላቅ ኃይሉ አይድንም።+ 17  ፈረስ ያድነኛል* ብሎ መታመን ከንቱ ተስፋ ነው፤+ታላቅ ኃይሉ ለመዳን ዋስትና አይሆንም። 18  እነሆ፣ የይሖዋ ዓይን የሚፈሩትን፣ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን የሚጠባበቁትን በትኩረት ይመለከታል፤+ 19  ይህም እነሱን* ከሞት ለመታደግ፣በረሃብ ወቅትም እነሱን በሕይወት ለማኖር ነው።+ 20  ይሖዋን በተስፋ እንጠባበቃለን።* እሱ ረዳታችንና ጋሻችን ነው።+ 21  ልባችን በእሱ ሐሴት ያደርጋል፤በቅዱስ ስሙ እንታመናለንና።+ 22  ይሖዋ ሆይ፣ አንተን ስንጠባበቅ፣+ታማኝ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “እስትንፋስ።”
ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት ያሳዩት።”
ወይም “ምክር።”
ወይም “ሐሳብ።”
ወይም “ምክር ለዘላለም ይጸናል።”
ወይም “ድል ያጎናጽፈኛል።”
ወይም “ነፍሳቸውን።”
ወይም “ነፍሳችን ይሖዋን በተስፋ ትጠባበቃለች።”