መዝሙር 35:1-28

  • ዳዊት፣ አምላክ ከጠላት እጅ እንዲታደገው ያቀረበው ጸሎት

    • ጠላቶች ይባረራሉ (5)

    • በብዙ ሕዝብ መካከል አምላክን ማወደስ (18)

    • ያለ ምክንያት ጠሉኝ (19)

የዳዊት መዝሙር። 35  ይሖዋ ሆይ፣ ባላጋራዎቼን በመቃወም ተሟገትልኝ፤+የሚዋጉኝን ተዋጋቸው።+   ትንሹንና* ትልቁን ጋሻህን ያዝ፤+ለእኔ ለመከላከልም ተነስ።+   በሚያሳድዱኝ ላይ ጦርና መጥረቢያ* አንሳ።+ “የማድንህ እኔ ነኝ” በለኝ።*+   ሕይወቴን* የሚሹ ይፈሩ፤ ይዋረዱም።+ እኔን ለማጥፋት የሚያሴሩ ተዋርደው ያፈግፍጉ።   በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ ይሁኑ፤የይሖዋ መልአክም ያባርራቸው።+   የይሖዋ መልአክ ሲያሳድዳቸውመንገዳቸው በጨለማ የተዋጠና የሚያዳልጥ ይሁን።   ያላንዳች ምክንያት እኔን ለማጥመድ በስውር መረብ ዘርግተዋልና፤ያላንዳች ምክንያት ጉድጓድ ቆፍረውልኛል።*   ሳያስቡት ጥፋት ይምጣባቸው፤በስውር ያስቀመጡት መረብም እነሱኑ ይያዛቸው፤እዚያም ውስጥ ወድቀው ይጥፉ።+   እኔ ግን በይሖዋ ሐሴት አደርጋለሁ፤*በማዳን ሥራውም እጅግ ደስ ይለኛል። 10  አጥንቶቼ ሁሉ እንዲህ ይላሉ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ምስኪኑን ብርቱ ከሆኑት፣ምስኪኑንና ድሃውን ከሚዘርፏቸው ሰዎች ትታደጋለህ።”+ 11  ክፉ ምሥክሮች ቀረቡ፤+ምንም ስለማላውቀው ነገር ጠየቁኝ። 12  ለመልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤+ደግሞም ሐዘን ላይ ጣሉኝ።* 13  እኔ ግን እነሱ በታመሙ ጊዜ ማቅ ለበስኩ፤ራሴን* በጾም አጎሳቆልኩ፤ጸሎቴም መልስ ሳያገኝ በተመለሰ ጊዜ፣* 14  ለጓደኛዬ ወይም ለወንድሜ እንደማደርገው እየተንቆራጠጥኩ አለቀስኩ፤እናቱ ሞታበት እንደሚያለቅስ ሰው አንገቴን በሐዘን ደፋሁ። 15  እኔ ስደናቀፍ ግን እነሱ ደስ ብሏቸው ተሰበሰቡ፤አድብተው እኔን ለመምታት ተሰበሰቡ፤ዘነጣጠሉኝ፤ በነገር መጎንተላቸውንም አልተዉም። 16  ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በንቀት ያፌዙብኛል፤*በእኔ ላይ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ።+ 17  ይሖዋ ሆይ፣ ዝም ብለህ የምታየው እስከ መቼ ነው?+ ከሚሰነዝሩብኝ ጥቃት ታደገኝ፤*+ውድ ሕይወቴን* ከደቦል አንበሶች አድናት።+ 18  ያን ጊዜ በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤+በብዙ ሕዝብ መካከል አወድስሃለሁ። 19  ያላንዳች ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ እኔን አይተው እንዲፈነድቁ፣ያለምክንያት የሚጠሉኝ+ በተንኮል እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ።+ 20  የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣምና፤ከዚህ ይልቅ በምድሪቱ በሰላም በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ።+ 21  እኔን ለመወንጀል አፋቸውን ይከፍታሉ፤“እሰይ! እሰይ! ዓይናችን ይህን አየ” ይላሉ። 22  ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል።+ ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ 23  ለእኔ ጥብቅና ለመቆም ንቃ፤ ተነሳም፤ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ተሟገትልኝ። 24  ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤+በእኔ እንዲፈነድቁ አትፍቀድ። 25  በልባቸው “እሰይ! የተመኘነውን አገኘን”* አይበሉ። ደግሞም “ዋጥነው” አይበሉ።+ 26  እኔ ላይ በደረሰው ጉዳት የሚፈነድቁ ሁሉይፈሩ፣ ይዋረዱም። በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። 27  በእኔ ጽድቅ የሚደሰቱ ግን እልል ይበሉ፤ሁልጊዜም እንዲህ ይበሉ፦ “በአገልጋዩ ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ ከፍ ከፍ ይበል።”+ 28  በዚህ ጊዜ ምላሴ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+ቀኑን ሙሉም ያወድስሃል።+

የግርጌ ማስታወሻ

አብዛኛውን ጊዜ ቀስተኞች የሚይዙት ትንሽ ጋሻ።
ወይም “በሁለቱም በኩል ስለት ያለው መጥረቢያ፤ የውጊያ መጥረቢያ።”
ወይም “ነፍሴንም ‘የማድንሽ እኔ ነኝ’ በላት።”
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “ለነፍሴ ጉድጓድ ቆፍረውላታል።”
ወይም “ነፍሴ ግን በይሖዋ ሐሴት ታደርጋለች።”
ወይም “ነፍሴን ሐዘን ላይ ጣሏት።”
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “ወደ ጉያዬ በተመለሰ ጊዜ።”
“ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች ለምግብ ብለው ያፌዛሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሴን ታደግ።”
ቃል በቃል “አንድ ያለችኝን።” ነፍሱን ወይም ሕይወቱን ያመለክታል።
ወይም “እሰይ! ነፍሳችን ደስ አላት።”
ወይም “ምላሴ በጽድቅህ ላይ ያሰላስላል።”