መዝሙር 38:1-22

  • ንስሐ የገባ ሰው ያቀረበው ጸሎት

    • “በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ” (6)

    • ይሖዋ እሱን የሚጠባበቁ ሰዎችን ይሰማል (15)

    • ‘ኃጢአቴ አስጨንቆኝ ነበር’ (18)

የዳዊት ማህሌት፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል። 38  ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤ተናደህም አታርመኝ።+   ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭኖኛል።+   ከቁጣህ የተነሳ መላ ሰውነቴ ታመመ።* ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም።+   የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤+እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል።   ከሞኝነቴ የተነሳቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ።   በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ።   ውስጤ ተቃጠለ፤*መላ ሰውነቴ ታመመ።+   ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ።*   ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም። 10  ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል።+ 11  ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ። 12  ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔን መጉዳት የሚፈልጉም ስለ ጥፋት ያወራሉ፤+ቀኑን ሙሉ ተንኮል ሲሸርቡ ይውላሉ። 13  እኔ ግን እንደ ደንቆሮ አልሰማቸውም፤+እንደ ዱዳም አፌን አልከፍትም።+ 14  መስማት እንደማይችል፣በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ። 15  ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በተስፋ ተጠባብቄአለሁና፤+ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተም መልስ ሰጥተኸኛል።+ 16  “በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና። 17  ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም።+ 18  በደሌን ተናዘዝኩ፤+ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር።+ 19  ይሁንና ጠላቶቼ ብርቱዎችና* ኃያላን ናቸው፤*ያላንዳች ምክንያት የሚጠሉኝ ተበራከቱ። 20  ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር። 21  ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ። አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ 22  አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣እኔን ለመርዳት ፍጠን።+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “በሥጋዬ ላይ ጤነኛ ቦታ የለም።”
ቃል በቃል “መላ ወገቤ ተቃጠለ።”
ወይም “እጮኻለሁ።”
ወይም “ነፍሴን።”
ቃል በቃል “ሕያዋንና።”
“ይሁንና ከመሬት ተነስተው የሚጠሉኝ ብዙ ናቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።