መዝሙር 39:1-13

  • ሕይወት አጭር ነው

    • ሰው እንደ እስትንፋስ ነው (5, 11)

    • “እንባዬን ችላ አትበል” (12)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።*+ የዳዊት ማህሌት። 39  እኔ “በምላሴ ኃጢአት እንዳልፈጽም+አካሄዴን እጠብቃለሁ። ክፉ ሰው ከእኔ ጋር እስካለ ድረስአፌን ለመጠበቅ ልጓም አስገባለሁ”*+ አልኩ።   ዱዳ ሆንኩ፤ ደግሞም ዝም አልኩ፤+መልካም ነገር ከመናገር እንኳ ታቀብኩ፤ይሁንና ሥቃዬ ከባድ ነበር።*   ልቤ በውስጤ ነደደ።* ሳወጣ ሳወርድ* እንደ እሳት ነደድኩ። በዚህ ጊዜ በአንደበቴ እንዲህ አልኩ፦   “ይሖዋ ሆይ፣ መጨረሻዬ ምን እንደሚሆን፣የዕድሜዬም ርዝማኔ ምን ያህል እንደሆነ እንዳውቅ እርዳኝ፤+ይህም ሕይወቴ ምን ያህል አጭር እንደሆነ* አውቅ ዘንድ ነው።   በእርግጥም ቀኖቼን ጥቂት* አደረግካቸው፤+የሕይወት ዘመኔም በፊትህ ከምንም አይቆጠርም።+ አዎ፣ ሰው ሁሉ ምንም ነገር የማይነካው ቢመስልም እንኳ እንደ እስትንፋስ ነው።+ (ሴላ)   በእርግጥም ሰው ሁሉ የሚመላለሰው እንደ ጥላ ነው። ላይ ታች የሚለው* በከንቱ ነው። ማን እንደሚጠቀምበት ሳያውቅ ንብረት ያከማቻል።+   ይሖዋ ሆይ፣ ታዲያ ተስፋዬ ምንድን ነው? ተስፋዬ አንተ ብቻ ነህ።   ከፈጸምኩት በደል ሁሉ አድነኝ።+ ሞኝ ሰው እንዲሳለቅብኝ አትፍቀድ።   ዱዳ ሆንኩ፤ይህን ያደረግከው አንተ ስለሆንክ+አፌን መክፈት አልቻልኩም።+ 10  በእኔ ላይ ያመጣኸውን መቅሰፍት ከእኔ አርቅ። እጅህ ስለመታኝ ዛልኩ። 11  ሰውን በሠራው ስህተት የተነሳ በመቅጣት ታርመዋለህ፤+እንደ ውድ ሀብት የሚመለከታቸውን ነገሮች እንደ ብል ትበላበታለህ። በእርግጥም ሰው ሁሉ እንደ እስትንፋስ ነው።+ (ሴላ) 12  ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት አዳምጥ።+ እንባዬን ችላ አትበል። እኔ በአንተ ዘንድ የባዕድ አገር ሰው ነኝና፤+እንደ አባቶቼ አልፌ የምሄድ ተጓዥ* ነኝ።+ 13  ከመሞቴና ከሕልውና ውጭ ከመሆኔ በፊት፣ፊቴ እንዲፈካ በክፉ ዓይን አትየኝ።”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በማሰሪያ እሸብበዋለሁ።”
ወይም “ተቀሰቀሰ።”
ቃል በቃል “ጋለ።”
ወይም “በምቃትትበት ጊዜ።”
ወይም “አላፊ ጠፊ እንደሆንኩ።”
ቃል በቃል “ጋት።”
ቃል በቃል “የሚንጫጫው።”
ወይም “ሰፋሪ።”