መዝሙር 4:1-8

  • በአምላክ በመታመን የቀረበ ጸሎት

    • “ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ” (4)

    • “በሰላም እተኛለሁ” (8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት። 4  ጻድቅ አምላኬ ሆይ፣+ ስጣራ መልስልኝ። በምጨነቅበት ጊዜ ማምለጫ መንገድ* አዘጋጅልኝ። ቸርነት አሳየኝ፤ ጸሎቴንም ስማ።   እናንተ የሰው ልጆች፣ ክብሬን ወደ ውርደት የምትለውጡት እስከ መቼ ነው? ከንቱ ነገሮችን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? ሐሰትንስ የምትሹት እስከ መቼ ነው? (ሴላ)   ይሖዋ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ልዩ በሆነ መንገድ እንደሚይዘው እወቁ፤*ይሖዋ በጠራሁት ጊዜ ይሰማኛል።   ተቆጡ፤ ሆኖም ኃጢአት አትሥሩ።+ የምትናገሩትን በመኝታችሁ ላይ ሳላችሁ በልባችሁ ተናገሩ፤ ጸጥም በሉ። (ሴላ)   የጽድቅ መሥዋዕቶች አቅርቡ፤በይሖዋም ታመኑ።+   “መልካም ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች አሉ። ይሖዋ ሆይ፣ የፊትህን ብርሃን በላያችን አብራ።+   የተትረፈረፈ እህል ከሰበሰቡና አዲስ የወይን ጠጅ በብዛት ካመረቱ ሰዎች ይበልጥልቤ በሐሴት እንዲሞላ አደረግክ።   በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤+ይሖዋ ሆይ፣ ተረጋግቼ እንድኖር የምታደርገኝ አንተ ብቻ ነህና።+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ሰፊ ቦታ።”
ወይም “ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ይለያል፤ ለእሱ ታማኝ የሆነውን ሰው ለራሱ ይለያል።”