መዝሙር 48:1-14
መዝሙር። የቆሬ ልጆች+ ማህሌት።
48 ይሖዋ ታላቅ ነው፤በአምላካችን ከተማ፣ በቅዱስ ተራራው እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።
2 በከፍታ ቦታ ላይ ተውባ የምትታየው፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣+በስተ ሰሜን ርቃ የምትገኘው የጽዮን ተራራ ነች፤ደግሞም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነች።+
3 አምላክ በማይደፈሩ ማማዎቿ ውስጥአስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን አስመሥክሯል።+
4 እነሆ፣ ነገሥታት ተሰብስበዋልና፤*አንድ ላይ ሆነው ገሰገሱ።
5 ከተማዋን ባዩአት ጊዜ ተገረሙ።
ደንግጠውም ፈረጠጡ።
6 በዚያም በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤እንደምትወልድ ሴት ጭንቅ ያዛቸው።
7 የተርሴስን መርከቦች በምሥራቅ ነፋስ ሰባበርክ።
8 የሰማነውን ነገር፣ በሠራዊት ጌታ በይሖዋ ከተማይኸውም በአምላካችን ከተማ አሁን በገዛ ዓይናችን አይተናል።
አምላክ ለዘላለም ያጸናታል።+ (ሴላ)
9 አምላክ ሆይ፣ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነንስለ ታማኝ ፍቅርህ እናሰላስላለን።+
10 አምላክ ሆይ፣ እንደ ስምህ ሁሉ ውዳሴህምእስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳል።+
ቀኝ እጅህ በጽድቅ ተሞልቷል።+
11 ከፍርድህ የተነሳ የጽዮን ተራራ+ ደስ ይበላት፤የይሁዳ ከተሞችም* ሐሴት ያድርጉ።+
12 በጽዮን ዙሪያ ሂዱ፤ በዙሪያዋም ተጓዙ፤ማማዎቿን ቁጠሩ።+
13 የመከላከያ ግንቦቿን*+ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።
ለመጪዎቹ ትውልዶች መናገር ትችሉ ዘንድ፣የማይደፈሩ ማማዎቿን በሚገባ አጢኑ።
14 ይህ አምላክ፣ ለዘላለም አምላካችን ነውና።+
እስከ ወዲያኛው* ይመራናል።+