መዝሙር 5:1-12

  • ይሖዋ ለጻድቅ መጠጊያ ነው

    • አምላክ ክፋትን ይጠላል (4, 5)

    • “በጽድቅህ ምራኝ” (8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በኔሂሎት።* የዳዊት ማህሌት። 5  ይሖዋ ሆይ፣ ቃሌን አዳምጥ፤+መቃተቴን ልብ በል።   ንጉሤና አምላኬ ሆይ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና፣ለእርዳታ የማሰማውን ጩኸት በትኩረት አዳምጥ።   ይሖዋ ሆይ፣ በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤+ያሳሰበኝን ነገር በማለዳ ለአንተ እናገራለሁ፤+ በተስፋም እጠባበቃለሁ።   አንተ በክፋት የምትደሰት አምላክ አይደለህምና፤+ክፉ ሰው ከአንተ ጋር አይቀመጥም።+   እብሪተኛ ሰው በፊትህ አይቆምም። መጥፎ ምግባር ያላቸውን ሁሉ ትጠላለህ፤+   ውሸት የሚናገሩትን ታጠፋለህ።+ ይሖዋ ዓመፀኞችንና አታላዮችን* ይጸየፋል።+   እኔ ግን ታላቅ ከሆነው ታማኝ ፍቅርህ የተነሳ+ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤+አንተን በመፍራት* ቅዱስ ወደሆነው ቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ በዙሪያዬ ስላሉ በጽድቅህ ምራኝ፤ከመንገድህ ላይ እንቅፋቶችን አስወግድልኝ።+   የሚሉት ነገር ሁሉ ሊታመን አይችልም፤ውስጣቸው በተንኮል የተሞላ ነው።ጉሮሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤በምላሳቸው ይሸነግላሉ።*+ 10  አምላክ ግን ይፈርድባቸዋል፤የገዛ ራሳቸው ዕቅድ ለጥፋት ይዳርጋቸዋል።+ ከበደላቸው ብዛት የተነሳ ይባረሩ፤በአንተ ላይ ዓምፀዋልና። 11  አንተን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ ግን ሐሴት ያደርጋሉ፤+ምንጊዜም በደስታ እልል ይላሉ። ሊጎዷቸው ከሚፈልጉ ሰዎች ትጠብቃቸዋለህ፤ስምህን የሚወዱም በአንተ ሐሴት ያደርጋሉ። 12  ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ የሆነውን ሁሉ ትባርካለህና፤ሞገስህ እንደ ትልቅ ጋሻ ይሆንላቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ደም አፍሳሽና አታላይ የሆነን ሰው።”
ወይም “ለአንተ አክብሮታዊ ፍርሃት በማሳየት።”
ወይም “በለሰለሰ አንደበት ይናገራሉ።”