መዝሙር 50:1-23
የአሳፍ+ ማህሌት።
50 የአማልክት አምላክ የሆነው ይሖዋ+ ተናግሯል፤ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው* ድረስምድርን ይጠራል።
2 በውበቷ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን፣+ አምላክ ያበራል።
3 አምላካችን ይመጣል፤ ፈጽሞም ዝም ሊል አይችልም።+
በፊቱ የሚባላ እሳት አለ፤+በዙሪያውም ሁሉ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል።+
4 በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ፣+በላይ ያሉትን ሰማያትና ምድርን ይጠራል፤+
5 “በመሥዋዕት አማካኝነት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርጉትን፣+ታማኝ አገልጋዮቼን ወደ እኔ ሰብስቡ” ይላል።
6 ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤አምላክ ራሱ ፈራጅ ነውና።+ (ሴላ)
7 “ሕዝቤ ሆይ፣ ስማ፤ እኔም እናገራለሁ፤እስራኤል ሆይ፣ በአንተ ላይ እመሠክርብሃለሁ።+
እኔ አምላክ፣ አዎ አምላክህ ነኝ።+
8 በመሥዋዕቶችህም ሆነዘወትር በፊቴ ባሉት የሚቃጠሉ መባዎችህ የተነሳ አልወቅስህም።+
9 ከቤትህ ኮርማ፣ከጉረኖህም ፍየሎች* መውሰድ አያስፈልገኝም።+
10 በጫካ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳት ሁሉ፣በሺህ ተራሮች ላይ ያሉ አራዊትም እንኳ የእኔ ናቸውና።+
11 በተራሮች ላይ የሚኖሩትን ወፎች ሁሉ አውቃለሁ፤+በመስክ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው እንስሳት የእኔ ናቸው።
12 ብራብ እንኳ ለአንተ አልነግርህም፤ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የእኔ ነውና።+
13 የኮርማዎችን ሥጋ እበላለሁ?የፍየሎችንስ ደም እጠጣለሁ?+
14 ምስጋናን ለአምላክ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤+ስእለትህንም ለልዑሉ አምላክ ስጥ፤+
15 በጭንቅ ቀን ጥራኝ።+
እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታወድሰኛለህ።”+
16 ክፉውን ግን አምላክ እንዲህ ይለዋል፦
“ስለ ሥርዓቴ ለማውራት፣ወይም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳኔ ለመናገር ምን መብት አለህ?+
17 ተግሣጼን* ትጠላለህና፤ለቃሌም ጀርባህን ትሰጣለህ።*+
18 ሌባ ስታይ ትደግፈዋለህ፤*+ከአመንዝሮችም ጋር ትወዳጃለህ።
19 አንደበትህን ክፉ ወሬ ለመንዛት ትጠቀምበታለህ፤ማታለያም ከምላስህ አይጠፋም።+
20 ከሌሎች ጋር ተቀምጠህ ወንድምህን ታማለህ፤+የገዛ እናትህን ልጅ ድክመት ታወራለህ።*
21 እነዚህን ሁሉ ነገሮች ስታደርግ፣ ዝም አልኩ፤በመሆኑም እንደ አንተ የምሆን መስሎህ ነበር።
አሁን ግን እወቅስሃለሁ፤ከአንተ ጋር ያለኝንም ሙግት አሳውቃለሁ።+
22 እናንተ አምላክን የምትረሱ፣ እባካችሁ ይህን ልብ በሉ፤+አለዚያ ብትንትናችሁን አወጣለሁ፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም።
23 ምስጋናን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤+ደግሞም ትክክለኛውን መንገድ በጥብቅ የሚከተልን ሰው፣የአምላክን ማዳን እንዲያይ አደርገዋለሁ።”+