መዝሙር 51:1-19

  • ንስሐ የገባ ሰው ጸሎት

    • ‘እናቴ በኃጢአት ፀነሰችኝ’ (5)

    • “ከኃጢአቴ አንጻኝ” (7)

    • “ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ” (10)

    • የተደቆሰ ልብ አምላክን ያስደስተዋል (17)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። ከቤርሳቤህ ጋር ግንኙነት ከፈጸመ በኋላ ነቢዩ ናታን መጥቶ ባነጋገረው ጊዜ ዳዊት ያቀረበው ማህሌት።+ 51  አምላክ ሆይ፣ እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን ሞገስ አሳየኝ።+ እንደ ታላቅ ምሕረትህ መተላለፌን ደምስስ።+   ከበደሌ ሙሉ በሙሉ እጠበኝ፤+ከኃጢአቴም አንጻኝ።+   መተላለፌን በሚገባ አውቃለሁና፤ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነው።*+   አንተን፣ አዎ ከማንም በላይ አንተን* በደልኩ፤+በአንተ ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር ፈጸምኩ።+ ስለዚህ አንተ በምትናገርበት ጊዜ ጻድቅ ነህ፤በምትፈርድበት ጊዜም ትክክል ነህ።+   እነሆ፣ በደለኛ ሆኜ ተወለድኩ፤እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ።*+   ከልብ የመነጨ እውነት ደስ ያሰኝሃል፤+ልቤን* እውነተኛ ጥበብ አስተምረው።   ንጹሕ እሆን ዘንድ በሂሶጵ ከኃጢአቴ አንጻኝ፤+ከበረዶም የበለጠ እነጣ ዘንድ እጠበኝ።+   ያደቀቅካቸው አጥንቶች ደስ እንዲላቸው፣+የደስታንና የሐሴትን ድምፅ አሰማኝ።   ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤*+የፈጸምኳቸውንም ስህተቶች ሁሉ አስወግድ።*+ 10  አምላክ ሆይ፣ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤+በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር።+ 11  ከፊትህ አትጣለኝ፤ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድ። 12  የአንተ ማዳን የሚያስገኘውን ደስታ መልስልኝ፤+አንተን የመታዘዝ ፍላጎት በውስጤ እንዲቀሰቀስ አድርግ።* 13  ኃጢአተኞች ወደ አንተ እንዲመለሱ፣ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ።+ 14  አምላክ ሆይ፣ የመዳኔ አምላክ፣+ አንደበቴ ጽድቅህን በደስታ ያስታውቅ ዘንድ+የደም ባለዕዳ ከመሆን አድነኝ።+ 15  ይሖዋ ሆይ፣ አፌ ምስጋናህን እንዲያውጅከንፈሮቼን ክፈት።+ 16  መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትፈልግምና፤ ቢሆንማ ኖሮ ባቀረብኩልህ ነበር፤+ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አያስደስትህም።+ 17  አምላክን የሚያስደስተው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤አምላክ ሆይ፣ የተሰበረንና የተደቆሰን ልብ ችላ አትልም።*+ 18  በበጎ ፈቃድህ ለጽዮን መልካም ነገር አድርግላት፤የኢየሩሳሌምን ግንቦች ገንባ። 19  በዚያን ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕቶች፣የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና ሙሉ በሙሉ የሚቀርቡ መባዎች ደስ ያሰኙሃል፤በዚያን ጊዜ ኮርማዎች በመሠዊያህ ላይ ይቀርባሉ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ከአእምሮዬ አይጠፋም።”
ቃል በቃል “አንተን ብቻ።”
ወይም “እናቴ ከፀነሰችኝ ጊዜ አንስቶ ኃጢአተኛ ነኝ።”
ወይም “የውስጥ ሰውነቴን።”
ወይም “ሰውር።”
ወይም “ደምስስ።”
ቃል በቃል “በፈቃደኝነት መንፈስ ደግፈኝ።”
ወይም “አትንቅም።”