መዝሙር 52:1-9

  • በአምላክ ታማኝ ፍቅር መታመን

    • በክፋት የሚኩራሩ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው (1-5)

    • ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በሀብት ይታመናሉ (7)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል ሄዶ፣ ዳዊት ወደ አሂሜሌክ ቤት መጥቶ እንደነበር በነገረው ጊዜ።+ 52  አንተ ኃያል፣ መጥፎ በሆነው ተግባርህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?+ የአምላክ ታማኝ ፍቅር ዘላቂ እንደሆነ አታውቅም?+   ምላስህ እንደ ምላጭ የተሳለ ነው፤+ጥፋትን ይሸርባል፤ ተንኮልንም ያቀነባብራል።+   መልካም ከሆነው ነገር ይልቅ ክፋትን፣ትክክል የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ትወዳለህ። (ሴላ)   አንተ አታላይ ምላስ!ጎጂ ቃልን ሁሉ ትወዳለህ።   በመሆኑም አምላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኩትሃል፤+መንጭቆ ይወስድሃል፤ ከድንኳንህም ጎትቶ ያወጣሃል፤+ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል።+ (ሴላ)   ጻድቃንም ይህን አይተው በፍርሃት* ይዋጣሉ፤+በእሱም ላይ ይስቃሉ።+   “እንዲህ ያለ ሰው አምላክን መጠጊያው* አያደርግም፤+ይልቁንም በታላቅ ሀብቱ ይታመናል፤+ራሱ በሚጠነስሰውም ሴራ* ይመካል።”*   እኔ ግን በአምላክ ቤት እንዳለ የለመለመ የወይራ ዛፍ እሆናለሁ፤ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር እታመናለሁ።+   እርምጃ ስለወሰድክ ለዘላለም አወድስሃለሁ፤+መልካም ነውና፣ በታማኝ አገልጋዮችህ ፊትበስምህ ተስፋ አደርጋለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “በአክብሮታዊ ፍርሃት።”
ወይም “ምሽጉ።”
ቃል በቃል “ራሱ በሚያመጣው መከራ።”
ወይም “ይጠለላል።”