መዝሙር 53:1-6
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በማሃላት ቅኝት።* ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።
53 ሞኝ* ሰው በልቡ
“ይሖዋ የለም” ይላል።+
የዓመፅ ድርጊታቸው ብልሹና አስጸያፊ ነው፤መልካም የሚሠራ ማንም የለም።+
2 ሆኖም ጥልቅ ማስተዋል ያለውና ይሖዋን የሚፈልግ ሰው ይኖር እንደሆነ ለማየት+አምላክ ከሰማይ ሆኖ ወደ ሰው ልጆች ይመለከታል።+
3 ሁሉም ወደ ሌላ ዞር ብለዋል፤ሁሉም ብልሹ ናቸው።
መልካም የሚሠራ ማንም የለም፤አንድ እንኳ የለም።+
4 ከክፉ አድራጊዎቹ መካከል አንዳቸውም አያስተውሉም?
ምግብ እንደሚበሉ ሕዝቤን ይውጣሉ።
ይሖዋን አይጠሩም።+
5 ይሁንና በታላቅ ሽብር፣ከዚህ በፊት ተሰምቷቸው በማያውቅ ታላቅ ፍርሃት ይዋጣሉ፤*በአንተ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩትን* ሰዎች አጥንት አምላክ ይበታትነዋልና።
ይሖዋ ስላልተቀበላቸው አንተ ታዋርዳቸዋለህ።
6 የእስራኤል መዳን ምነው ከጽዮን በመጣ!+
ይሖዋ የተማረከውን ሕዝቡን በሚመልስበት ጊዜ፣ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤል ሐሴት ያድርግ።
የግርጌ ማስታወሻ
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ማመዛዘን የጎደለው።”
^ “የሚያስፈራ ነገር በሌለበት በፍርሃት ይዋጣሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ቃል በቃል “በዙሪያህ የሰፈሩትን።”