መዝሙር 54:1-7

  • ዳዊት በጠላቶቹ መካከል ሳለ እርዳታ ለማግኘት ያቀረበው ጸሎት

    • “አምላክ ረዳቴ ነው” (4)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዚፍ ሰዎች ወደ ሳኦል መጥተው “ዳዊት እኛ ጋ ተደብቋል” ባሉት ጊዜ ዳዊት የዘመረው መዝሙር።+ 54  አምላክ ሆይ፣ በስምህ አድነኝ፤+በኃይልህም ደግፈኝ።*+   አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+ለአፌም ቃል ትኩረት ስጥ።   ባዕዳን በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤ጨካኝ ሰዎችም ሕይወቴን* ይሻሉ።+ ስለ አምላክ ምንም ግድ የላቸውም።*+ (ሴላ)   እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤+ይሖዋ እኔን* ከሚደግፉ ጋር ነው።   የገዛ ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ ይመልስባቸዋል፤+በታማኝነትህ አስወግዳቸው።*+   ለአንተ በፈቃደኝነት መሥዋዕት አቀርባለሁ።+ ይሖዋ ሆይ፣ መልካም ነውና፣ ስምህን አወድሳለሁ።+   ከጭንቅ ሁሉ ያድነኛልና፤+ጠላቶቼንም በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ተሟገትልኝ።”
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “አምላክን በፊታቸው አላደረጉትም።”
ወይም “ነፍሴን።”
ቃል በቃል “ዝም አሰኛቸው።”