መዝሙር 55:1-23
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር።
55 አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+ምሕረት እንድታደርግልኝ የማቀርበውንም ልመና ቸል አትበል።*+
2 ትኩረት ስጠኝ፤ መልስልኝም።+
ያሳሰበኝ ጉዳይ እረፍት ነስቶኛል፤+ደግሞም በጣም ተጨንቄአለሁ፤
3 ይህም ጠላት ከሚናገረው ቃል፣ክፉውም ሰው ከሚያሳድረው ጫና የተነሳ ነው።
እነሱ በእኔ ላይ መከራ ይከምራሉና፤በቁጣም ተሞልተው በጥላቻ ዓይን ያዩኛል።+
4 ልቤ በውስጤ በጣም ተጨነቀ፤+የሞት ፍርሃትም ዋጠኝ።+
5 ፍርሃት አደረብኝ፤ ደግሞም ተንቀጠቀጥኩ፤ብርክም ያዘኝ።
6 እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “ምነው እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝ!
በርሬ ሄጄ ያለስጋት በኖርኩ ነበር።
7 እነሆ፣ ወደ ሩቅ ቦታ በበረርኩ፣+
በምድረ በዳም በቆየሁ ነበር።+ (ሴላ)
8 ከአውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼመጠለያ ወደማገኝበት ቦታ ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።”
9 ይሖዋ ሆይ፣ ግራ አጋባቸው፤ ዕቅዳቸውንም አጨናግፍ፤+በከተማዋ ውስጥ ዓመፅና ብጥብጥ አይቻለሁና።
10 ቅጥሮቿ ላይ ወጥተው ቀንና ሌሊት ይዞራሉ፤በውስጧም ተንኮልና መከራ አለ።+
11 ጥፋት በመካከሏ አለ፤ጭቆናና ማታለል ከአደባባይዋ ፈጽሞ አይጠፉም።+
12 የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤+ቢሆንማ ኖሮ በቻልኩት ነበር።
በእኔ ላይ የተነሳው ባላጋራ አይደለም፤ቢሆንማ ኖሮ ከእሱ በተሸሸግኩ ነበር።
13 ነገር ግን ይህን ያደረግከው እንደ እኔው ሰው* የሆንከው አንተ ነህ፤+በሚገባ የማውቅህ የገዛ ጓደኛዬ ነህ።+
14 በመካከላችን የጠበቀ ወዳጅነት ነበር፤ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ አምላክ ቤት አብረን እንሄድ ነበር።
15 ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው!+
በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር* ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና።
16 እኔ በበኩሌ አምላክን እጣራለሁ፤ይሖዋም ያድነኛል።+
17 በማታ፣ በጠዋትና በቀትር እጨነቃለሁ፤ ደግሞም እቃትታለሁ፤*+እሱም ድምፄን ይሰማል።+
18 በእኔ ላይ ጦርነት ከከፈቱ ሰዎች ይታደገኛል፤* ሰላም እንዳገኝም ያደርጋል፤እጅግ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋልና።+
19 ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አምላክ+ ይሰማል፤ምላሽም ይሰጣቸዋል።+ (ሴላ)
አምላክን የማይፈሩት እነዚህ ሰዎች+ለመለወጥ ፈቃደኞች አይደሉም።
20 ከእሱ* ጋር ሰላም በነበራቸው ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል፤+የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሷል።+
21 የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ።
ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑምእንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+
22 ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤+እሱም ይደግፍሃል።+
ጻድቁ እንዲወድቅ* ፈጽሞ አይፈቅድም።+
23 አምላክ ሆይ፣ አንተ ግን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ።+
የደም ዕዳ ያለባቸውና አታላይ የሆኑ ሰዎች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም።+
እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።