መዝሙር 56:1-13
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ራቅ ባለ ቦታ የምትገኝ ዝምተኛ ርግብ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* ፍልስጤማውያን በጌት በያዙት ጊዜ።+
56 አምላክ ሆይ፣ ሟች የሆነ ሰው ጥቃት እየሰነዘረብኝ* ስለሆነ ሞገስ አሳየኝ።
ቀኑን ሙሉ ይዋጉኛል፤ ደግሞም ያስጨንቁኛል።
2 ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ እኔን ለመንከስ ይሞክራሉ፤ብዙዎች በእብሪት ተነሳስተው ይዋጉኛል።
3 ፍርሃት በሚሰማኝ ጊዜ+ በአንተ እታመናለሁ።+
4 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።
ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+
5 ቀኑን ሙሉ የእኔን ጉዳይ ለማበላሸት ይጥራሉ፤ሐሳባቸው እኔን መጉዳት ብቻ ነው።+
6 እኔን ለማጥቃት ራሳቸውን ይሰውራሉ፤ሕይወቴን* ለማጥፋት በመሻት+እርምጃዬን አንድ በአንድ ይከታተላሉ።+
7 ከክፋታቸው የተነሳ አስወግዳቸው።
አምላክ ሆይ፣ ብሔራትን በቁጣህ አጥፋቸው።+
8 ከቦታ ቦታ ስንከራተት አንድ በአንድ ትከታተላለህ።+
እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም።+
ደግሞስ በመጽሐፍህ ውስጥ ሰፍሮ የለም?+
9 እርዳታ ለማግኘት በምጣራበት ቀን ጠላቶቼ ያፈገፍጋሉ።+
አምላክ ከጎኔ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።+
10 ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣ቃሉን በማወድሰው በይሖዋ፣
11 አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም።+
ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?+
12 አምላክ ሆይ፣ ለአንተ በተሳልኳቸው ስእለቶች የተነሳ ግዴታ ውስጥ ገብቻለሁ፤+ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ።+
13 አንተ ከሞት ታድገኸኛልና፤*+እግሮቼንም ከእንቅፋት አድነሃል፤+ይህም በሕያዋን ብርሃን በአምላክ ፊት እመላለስ ዘንድ ነው።+