መዝሙር 58:1-11

  • በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ

    • ክፉዎች እንዲቀጡ የቀረበ ጸሎት (6-8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት። የዳዊት መዝሙር። ሚክታም።* 58  እናንተ የሰው ልጆች፣ ዝም ብላችሁ እያለ ስለ ጽድቅ ልትናገሩ ትችላላችሁ?+ በቅንነትስ መፍረድ ትችላላችሁ?+   ይልቁንም በልባችሁ ክፋት ትጠነስሳላችሁ፤+እጆቻችሁም በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ያስፋፋሉ።+   ክፉዎች፣ ከተወለዱበት ጊዜ* ጀምሮ መንገድ ስተዋል፤*ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ ሥርዓት የሌላቸውና ውሸታሞች ናቸው።   መርዛቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤+ጆሮውን እንደ ደፈነ ጉበና* ደንቆሮ ናቸው።   ድግምተኞቹ ምንም ያህል ችሎታ ቢኖራቸውጉበናው ድምፃቸውን አይሰማም።   አምላክ ሆይ፣ ጥርሳቸውን ከአፋቸው አርግፍ! ይሖዋ ሆይ፣ የእነዚህን አንበሶች* መንጋጋ ሰባብር!   ፈስሶ እንደሚያልቅ ውኃ ይጥፉ። አምላክ ደጋኑን ወጥሮ በቀስቶቹ ይጣላቸው።   ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ፀሐይን ፈጽሞ እንደማያይ ከሴት የተወለደ ጭንጋፍ ይሁኑ።   በእሳት የተቀጣጠለው እሾህ ድስታችሁን ሳያሞቀው፣አምላክ እርጥቡንም ሆነ የሚነደውን ቅርንጫፍ እንደ አውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደዋል።+ 10  ጻድቅ ሰው በክፉዎች ላይ የተወሰደውን የበቀል እርምጃ በማየቱ ደስ ይለዋል፤+እግሮቹ በእነሱ ደም ይርሳሉ።+ 11  በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል።+ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ተበላሽተዋል።”
ቃል በቃል “ከማህፀን።”
በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።
ወይም “ደቦል አንበሶች።”