መዝሙር 6:1-10
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በሸሚኒት ቅኝት፣* በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። የዳዊት ማህሌት።
6 ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤በታላቅ ቁጣህም አታርመኝ።+
2 ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ።*
ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።+
3 አዎ፣ እጅግ ተረብሻለሁ፤*+ይሖዋ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ድረስ ነው? ብዬ እጠይቅሃለሁ።+
4 ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ፤ ደግሞም ታደገኝ፤*+ለታማኝ ፍቅርህ ስትል አድነኝ።+
5 ሙታን አንተን አያነሱም፤*በመቃብር* ማን ያወድስሃል?+
6 ከመቃተቴ የተነሳ ዝያለሁ፤+ሌሊቱን ሙሉ መኝታዬን በእንባ አርሳለሁ፤*በለቅሶ አልጋዬን አጥለቀልቃለሁ።+
7 በሐዘኔ ምክንያት ዓይኔ ደክሟል፤+ከሚያጠቁኝ ሰዎች ሁሉ የተነሳ ዓይኔ ፈዟል።*
8 እናንተ መጥፎ ምግባር ያላችሁ ሁሉ ከእኔ ራቁ፤ይሖዋ የለቅሶዬን ድምፅ ይሰማልና።+
9 ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ የማቀርበውን ልመና ይሰማል፤+ይሖዋ ጸሎቴን ይቀበላል።
10 ጠላቶቼ በሙሉ ያፍራሉ፤ ደግሞም እጅግ ይደነግጣሉ፤በድንገት ውርደት ተከናንበው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።+
የግርጌ ማስታወሻ
^ የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ምሕረት አድርግልኝ።”
^ ወይም “ነፍሴ እጅግ ተረብሻለች።”
^ ወይም “ነፍሴን ታደጋት።”
^ ወይም “አያስታውሱም።”
^ ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ቃል በቃል “አልጋዬ እንዲዋኝ አደርጋለሁ።”
^ ወይም “አርጅቷል።”