መዝሙር 60:1-12

  • አምላክ ጠላቶችን አሸነፈ

    • “የሰው ማዳን ከንቱ ነው” (11)

    • “አምላክ ኃይል ይሰጠናል” (12)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በማስታወሻ አበባ” የሚዘመር። ሚክታም።* የዳዊት መዝሙር። ለትምህርት። ከአራምናሃራይም እና ከአራምጾባ ሰዎች ጋር በተዋጋ ጊዜ፤ ኢዮዓብም ተመልሶ በጨው ሸለቆ 12,000 ኤዶማውያንን ፈጀ።+ 60  አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ አድርገኸናል፤ መከላከያዎቻችንን ጥሰህ አልፈሃል።+ ተቆጥተኸናል፤ አሁን ግን መልሰህ ተቀበለን!   ምድርን አናወጥካት፤ ሰነጣጠቅካት። እየፈራረሰች ነውና ስንጥቆቿን ጠግን።   ሕዝብህ መከራ እንዲደርስበት አደረግክ። የወይን ጠጅ እንድንጠጣና እንድንንገዳገድ አደረግከን።+   አንተን የሚፈሩ ከቀስት መሸሽና ማምለጥ እንዲችሉምልክት አቁምላቸው።* (ሴላ)   የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠን።+   አምላክ በቅድስናው* እንዲህ ብሏል፦ “ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤+የሱኮትንም ሸለቆ* አከፋፍላለሁ።+   ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤+ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤*ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።+   ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው።+ በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ።+ በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”+   ወደተከበበችው* ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?+ 10  አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።+ 11  ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።+ 12  አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤+ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻ

“አቆምክላቸው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“በቅዱስ ስፍራው” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”
ቃል በቃል “ለራሴ ምሽግ ነው።”
“ወደተመሸገችው” ማለትም ሊሆን ይችላል።