መዝሙር 62:1-12

  • እውነተኛ መዳን የሚገኘው ከአምላክ ነው

    • “ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ” (1, 5)

    • ‘ልባችሁን በአምላክ ፊት አፍስሱ’ (8)

    • ሰዎች እስትንፋስ ናቸው (9)

    • በሀብት አትታመኑ (10)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።* የዳዊት ማህሌት። 62  ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ።* መዳን የማገኘው ከእሱ ዘንድ ነው።+   በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤+ከልክ በላይ አልናወጥም።+   አንድን ሰው ለመግደል ጥቃት የምትሰነዝሩበት እስከ መቼ ነው?+ ሁላችሁም እንዳዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ እንደተቃረበም የድንጋይ ቅጥር አደገኛ ናችሁ።*   ካለበት ከፍ ያለ ቦታ ሊጥሉት* እርስ በርሳቸው ይማከራሉና፤በመዋሸት ደስ ይሰኛሉ። በአፋቸው ይባርካሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ።+ (ሴላ)   ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ፤*+ምክንያቱም ተስፋዬ የሚመጣው ከእሱ ዘንድ ነው።+   በእርግጥም እሱ ዓለቴና አዳኜ እንዲሁም አስተማማኝ መጠጊያዬ ነው፤በምንም ዓይነት አልናወጥም።+   የእኔ መዳንና ክብር የተመካው በአምላክ ላይ ነው። እሱ ጠንካራ ዓለቴና መጠጊያዬ ነው።+   ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእሱ ታመኑ። ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ።+ አምላክ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ)   የሰው ልጆች እስትንፋስ ናቸው፤ሰዎች ከንቱ መመኪያ ናቸው።+ አንድ ላይ ሆነው በሚዛን ሲመዘኑ ከአየር እንኳ ይቀልላሉ።+ 10  በዝርፊያ አትታመኑ፤ወይም በስርቆት እጠቀማለሁ ብላችሁ በከንቱ ተስፋ አታድርጉ። ሀብታችሁ ቢበዛ ልባችሁን በእሱ ላይ አትጣሉ።+ 11  አምላክ አንድ ጊዜ ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፦ ብርታት የአምላክ ነው።+ 12  ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርም የአንተ ነው፤+ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍላለህና።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ነፍሴ ዝም ብላ አምላክን ትጠባበቃለች።”
“እሱ ያዘመመ ግንብ፣ ሊወድቅ የተቃረበም የድንጋይ ቅጥር የሆነ ይመስል ሁላችሁም የምታጠቁት እስከ መቼ ነው?” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት።”
ወይም “ነፍሴ ሆይ፣ አምላክን ዝም ብለሽ ተጠባበቂ።”