መዝሙር 64:1-10
-
ስውር ከሆኑ ጥቃቶች ጥበቃ ማግኘት
-
“አምላክ ይመታቸዋል” (7)
-
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
64 አምላክ ሆይ፣ የማቀርበውን ልመና ስማ።+
ጠላት ከሚሰነዝርብኝ አስፈሪ ጥቃት ሕይወቴን ታደግ።
2 ከክፉ ሰዎች ስውር ሴራ፣ከክፉ አድራጊዎች ሸንጎ ጠብቀኝ፤+
3 እነሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት ያነጣጥራሉ፤
4 ይህን የሚያደርጉት ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ለመምታት ነው፤ያላንዳች ፍርሃት በድንገት ይመቱታል።
5 ክፉ ዓላማቸውን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፤*በስውር እንዴት ወጥመድ እንደሚዘረጉ ይነጋገራሉ።
“ማን ያየዋል?” ይላሉ።+
6 ክፉ ነገር ለመሥራት አዳዲስ መንገዶች ይቀይሳሉ፤የረቀቀ ሴራቸውን በስውር ይሸርባሉ፤+በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ አይደረስበትም።
7 ሆኖም አምላክ ይመታቸዋል፤+እነሱም በድንገት በቀስት ይቆስላሉ።
8 የገዛ ምላሳቸው ለውድቀት ይዳርጋቸዋል፤+ይህን የሚመለከቱ ሁሉ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።
9 በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤አምላክ ያደረገውንም ነገር ያውጃሉ፤ሥራውንም በሚገባ ያስተውላሉ።+
10 ጻድቅ ሰው በይሖዋ ሐሴት ያደርጋል፤ እሱንም መጠጊያው ያደርጋል፤+ቀና ልብ ያላቸውም ሁሉ ይደሰታሉ።*