መዝሙር 65:1-13

  • አምላክ ምድርን ይንከባከባል

    • “ጸሎት ሰሚ” (2)

    • ‘አንተ የመረጥከው ሰው ደስተኛ ነው’ (4)

    • የአምላክ ጥሩነት (11)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት። መዝሙር። 65  አምላክ ሆይ፣ በጽዮን+ ውዳሴ ይቀርብልሃል፤የተሳልነውን ለአንተ እንሰጣለን።+   ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው* ወደ አንተ ይመጣል።+   የፈጸምኳቸው በደሎች አሸንፈውኛል፤+አንተ ግን መተላለፋችንን ይቅር አልክ።+   በቅጥር ግቢዎችህ ይኖር ዘንድየመረጥከውና ያቀረብከው ሰው ደስተኛ ነው።+ እኛም በቤትህ፣ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደስህ+ ውስጥ ባሉ ጥሩ ነገሮች እንረካለን።+   የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ፍርሃት* በሚያሳድሩ የጽድቅ ተግባሮች ትመልስልናለህ፤+በምድር ዳርቻዎች ሁሉናከባሕሩ ማዶ ርቀው ላሉት መታመኛቸው ነህ።+   አንተ* በኃይልህ ተራሮችን አጽንተህ መሥርተሃል፤ኃይልንም ለብሰሃል።+   አንተ* የሚናወጡትን ባሕሮች፣ የሞገዶቻቸውን ድምፅ፣የብሔራትንም ነውጥ ጸጥ ታሰኛለህ።+   ርቀው በሚገኙ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች ምልክቶችህን አይተው በታላቅ አድናቆት ይዋጣሉ፤+ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ያሉ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋለህ።   ምድርን እጅግ ፍሬያማ* በማድረግናበማበልጸግ ትንከባከባታለህ።+ የአምላክ ጅረት በውኃ የተሞላ ነው፤ለሰዎች እህል ትሰጣለህ፤+ምድርን ያዘጋጀኸው በዚህ መንገድ ነውና። 10  ትልሞቿን በውኃ ታረሰርሳለህ፤ የታረሰውንም መሬት* ትደለድላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳታለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።+ 11  ዘመኑ ጥሩነትህን እንደ ዘውድ እንዲጎናጸፍ ታደርጋለህ፤በጎዳናዎችህም ላይ የተትረፈረፉ ነገሮች ይፈስሳሉ።*+ 12  የምድረ በዳው የግጦሽ መሬቶች ሁልጊዜ እንደረሰረሱ ናቸው፤*+ኮረብቶቹም ደስታን ተጎናጽፈዋል።+ 13  የግጦሽ መሬቶቹ በመንጎች ተሞሉ፤ሸለቆዎቹም* በእህል ተሸፈኑ።+ በድል አድራጊነት እልል ይላሉ፤ አዎ፣ ይዘምራሉ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”
ወይም “አክብሮታዊ ፍርሃት።”
ቃል በቃል “እሱ።”
ቃል በቃል “እሱ።”
ቃል በቃል “እንድትጥለቀለቅ።”
ወይም “ጉብታዎቿንም።”
ቃል በቃል “ስብ ይንጠባጠባል።”
ቃል በቃል “ያንጠባጥባሉ።”
ወይም “ረባዳማ ሜዳዎቹም።”