መዝሙር 66:1-20

  • አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ የአምላክ ሥራዎች

    • “ኑና የአምላክን ሥራዎች ተመልከቱ” (5)

    • ‘ስእለቴን ለአንተ እፈጽማለሁ’ (13)

    • አምላክ ጸሎት ይሰማል (18-20)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። መዝሙር። ማህሌት። 66  ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለአምላክ እልል ትበል።+   ለክብራማ ስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ። ውዳሴውን አድምቁ።+   አምላክን እንዲህ በሉት፦ “ሥራዎችህ አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+ ከኃይልህ ታላቅነት የተነሳጠላቶችህ በፊትህ ይሽቆጠቆጣሉ።+   በምድር ያሉ ሁሉ ይሰግዱልሃል፤+ለአንተ የውዳሴ መዝሙር ይዘምራሉ፤ለስምህም የውዳሴ መዝሙር ይዘምራሉ።”+ (ሴላ)   ኑና የአምላክን ሥራዎች ተመልከቱ። ለሰው ልጆች ያከናወናቸው ተግባሮች አክብሮታዊ ፍርሃት የሚያሳድሩ ናቸው።+   እሱ ባሕሩን ደረቅ ምድር አደረገው፤+ወንዙን በእግራቸው ተሻገሩ።+ በዚያ በእሱ እጅግ ደስ አለን።+   በኃይሉ ለዘላለም ይገዛል።+ ዓይኖቹ ብሔራትን አተኩረው ያያሉ።+ ግትር የሆኑ ሰዎች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።+ (ሴላ)   እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አምላካችንን አወድሱ፤+ለእሱ የሚቀርበውም የውዳሴ ድምፅ ይሰማ።   እሱ በሕይወት ያኖረናል፤*+እግራችን እንዲደናቀፍ* አይፈቅድም።+ 10  አምላክ ሆይ፣ አንተ መርምረኸናልና፤+ብር በእሳት እንደሚጠራ ሁሉ አንተም እኛን አጥርተኸናል። 11  ማጥመጃ መረብ ውስጥ አስገባኸን፤በላያችንም* ከባድ ሸክም ጫንክብን። 12  ሟች ሰው ላያችን* ላይ እንዲጋልብ አደረግክ፤በእሳት መካከልና በውኃ መካከል አለፍን፤ከዚያም እረፍት ወደምናገኝበት ስፍራ አመጣኸን። 13  ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ ይዤ ወደ ቤትህ እመጣለሁ፤+ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤+ 14  ይህም በጭንቅ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ ከንፈሮቼ ቃል የገቡት፣አፌም የተናገረው ነው።+ 15  የሰቡ እንስሳትን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጌከሚጨስ የአውራ በጎች መሥዋዕት ጋር አቀርብልሃለሁ። ከአውራ ፍየሎችም ጋር ኮርማዎችን አቀርባለሁ። (ሴላ) 16  እናንተ አምላክን የምትፈሩ ሁሉ፣ ኑና አዳምጡ፤ለእኔ ያደረገልኝንም* ነገር እነግራችኋለሁ።+ 17  በአፌ ወደ እሱ ተጣራሁ፤በአንደበቴም ከፍ ከፍ አደረግኩት። 18  በልቤ አንዳች መጥፎ ነገር ይዤ ቢሆን ኖሮ፣ይሖዋ ባልሰማኝ ነበር።+ 19  ሆኖም አምላክ ሰምቷል፤+ጸሎቴን በትኩረት አዳምጧል።+ 20  ጸሎቴን ከመስማት ጆሮውን ያልመለሰ፣ደግሞም ታማኝ ፍቅሩን ያልነፈገኝ አምላክ ውዳሴ ይድረሰው።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ነፍሳችንን በሕይወት ያቆያታል።”
ወይም “እንዲንገዳገድ፤ እንዲውተረተር።”
ቃል በቃል “በዳሌዎቻችንም ላይ።”
ቃል በቃል “ራሳችን።”
ወይም “ለነፍሴ ያደረገላትንም።”