መዝሙር 70:1-5
-
አፋጣኝ እርዳታ ለማግኘት የቀረበ ልመና
-
“ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ” (5)
-
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት መዝሙር፤ ማስታወሻ ሆኖ የሚያገለግል።*
70 አምላክ ሆይ፣ አድነኝ፤ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+
2 ሕይወቴን* ለማጥፋት የሚሹኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።
በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙአፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።
3 “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ
አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ።
4 አንተን የሚፈልጉ ግንበአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ።+
የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣
ምንጊዜም “አምላክ ታላቅ ይሁን!” ይበሉ።
5 እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤+አምላክ ሆይ፣ ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ።+
አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤+ይሖዋ ሆይ፣ አትዘግይ።+