መዝሙር 71:1-24

  • በዕድሜ የገፉ ሰዎች ያላቸው የመተማመን ስሜት

    • ከልጅነት ጀምሮ በአምላክ መታመን (5)

    • ‘ጉልበቴ በሚያልቅበት ጊዜ አትተወኝ’ (9)

    • ‘አምላክ ከልጅነቴ ጀምሮ አስተምሮኛል’ (17)

71  ይሖዋ ሆይ፣ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁ። ፈጽሞ ለኀፍረት አልዳረግ።+   በጽድቅህ አድነኝ፤ ታደገኝም። ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤* አድነኝም።+   ምንጊዜም የምገባበትመሸሸጊያ ዓለት ሁንልኝ። አንተ ቋጥኜና ምሽጌ ስለሆንክእኔን ለማዳን ትእዛዝ ስጥ።+   አምላኬ ሆይ፣ ከክፉው እጅ፣ግፈኛ ከሆነው ጨቋኝ ሰው መዳፍ ታደገኝ።+   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ተስፋዬ ነህ፤ከልጅነቴ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ።*+   ከተወለድኩበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ታምኛለሁ፤ከእናቴ ማህፀን ያወጣኸኝ አንተ ነህ።+ ሁልጊዜ አወድስሃለሁ።   ለብዙዎች መደነቂያ ሆንኩ፤አንተ ግን ጽኑ መጠጊያዬ ነህ።   አፌ በውዳሴህ ተሞልቷል፤+ቀኑን ሙሉ ስለ ግርማህ እናገራለሁ።   በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤+ጉልበቴ በሚያልቅበት ጊዜም አትተወኝ።+ 10  ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ይናገራሉ፤ሕይወቴን* የሚሹ ሰዎችም በእኔ ላይ ሴራ ይጠነስሳሉ፤+ 11  እንዲህም ይላሉ፦ “አምላክ ትቶታል። የሚያድነው ስለሌለ አሳዳችሁ ያዙት።”+ 12  አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ። አምላኬ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን።+ 13  የሚቃወሙኝ* ሰዎችይፈሩ፤ ይጥፉም።+ የእኔን ጥፋት የሚሹውርደትና ኀፍረት ይከናነቡ።+ 14  እኔ ግን አንተን መጠባበቄን እቀጥላለሁ፤በውዳሴ ላይ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ። 15  አፌ ስለ ጽድቅህ ያወራል፤+ከብዛታቸው የተነሳ ላውቃቸው* ባልችልም እንኳአንደበቴ ስለ ማዳን ሥራዎችህ ቀኑን ሙሉ ይናገራል።+ 16  ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣መጥቼ ስለ ብርቱ ሥራዎችህ እናገራለሁ፤ስለ አንተ ጽድቅ ብቻ እናገራለሁ። 17  አምላክ ሆይ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ አስተምረኸኛል፤+እኔም እስካሁን ድረስ ድንቅ ሥራዎችህን አስታውቃለሁ።+ 18  አምላክ ሆይ፣ ሳረጅና ስሸብትም እንኳ አትጣለኝ።+ ለቀጣዩ ትውልድ ስለ ብርታትህ፣*ገና ለሚመጡትም ሁሉ ስለ ኃያልነትህ ልናገር።+ 19  አምላክ ሆይ፣ ጽድቅህ እጅግ ታላቅ ነው፤+ታላላቅ ነገሮችን አከናውነሃል፤አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?+ 20  ብዙ ጭንቅና መከራ ብታሳየኝም እንኳ+እንደገና እንዳንሰራራ አድርገኝ፤ጥልቅ ከሆነው ምድር* አውጣኝ።+ 21  ታላቅነቴ ገናና እንዲሆን አድርግ፤ዙሪያዬንም ከበህ አጽናናኝ። 22  እኔም አምላኬ ሆይ፣ ከታማኝነትህ+ የተነሳበባለ አውታር መሣሪያ አወድስሃለሁ። የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣በበገና የውዳሴ መዝሙር እዘምርልሃለሁ። 23  ለአንተ የውዳሴ መዝሙር በምዘምርበት ጊዜ ከንፈሮቼ እልል ይላሉ፤+ሕይወቴን አድነሃታልና።*+ 24  ምላሴ ቀኑን ሙሉ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤*+የእኔን መጥፋት የሚሹ ሰዎች ያፍራሉና፤ ደግሞም ይዋረዳሉ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ጎንበስ ብለህ ስማኝ።”
ወይም “አንተ መመኪያዬ ነህ።”
ወይም “ነፍሴን።”
ወይም “ነፍሴን የሚቃወሟት።”
ወይም “ልቆጥራቸው።”
ቃል በቃል “ስለ ክንድህ።”
ወይም “በምድር ካሉ ጥልቅ ውኃዎች።”
ወይም “ነፍሴን ዋጅተሃታልና።”
ወይም “ያሰላስላል።”