መዝሙር 74:1-23
ማስኪል።* የአሳፍ+ መዝሙር።
74 አምላክ ሆይ፣ ለዘላለም የጣልከን ለምንድን ነው?+
በመስክህ በተሰማራው መንጋ ላይ ቁጣህ የነደደው* ለምንድን ነው?+
2 ከረጅም ዘመን በፊት የራስህ ያደረግከውን ሕዝብ፣*+ርስትህ አድርገህ የዋጀኸውን ነገድ አስታውስ።+
የኖርክበትን የጽዮን ተራራ+ አስብ።
3 ለዘለቄታው ወደፈራረሰው ቦታ አቅና።+
ጠላት በቅዱሱ ስፍራ ያለውን ነገር ሁሉ አጥፍቷል።+
4 ጠላቶችህ በመሰብሰቢያ ቦታህ* ውስጥ በድል አድራጊነት ጮኹ።+
በዚያም የራሳቸውን ዓርማ ምልክት አድርገው አቆሙ።
5 መጥረቢያቸውን ይዘው ጥቅጥቅ ያሉ ደኖችን እንደሚጨፈጭፉ ሰዎች ናቸው።
6 በቅርጻ ቅርጾች ያጌጡትን+ ግድግዳዎች በጠቅላላ በመጥረቢያና በብረት ዘንግ አፈራረሱ።
7 መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ።+
ስምህ የተጠራበትን የማደሪያ ድንኳን መሬት ላይ ጥለው አረከሱት።
8 እነሱም ሆኑ ዘሮቻቸው በልባቸው
“በምድሪቱ ላይ ያሉት የአምላክ መሰብሰቢያ* ቦታዎች በሙሉ ይቃጠሉ” ብለዋል።
9 የምናያቸው ምልክቶች የሉም፤አንድም የቀረ ነቢይ የለም፤ደግሞም ይህ እስከ መቼ እንደሚቀጥል ከእኛ መካከል የሚያውቅ የለም።
10 አምላክ ሆይ፣ ባላጋራ የሚሳለቀው እስከ መቼ ነው?+
ጠላት ስምህን ለዘላለም እያቃለለ ይኖራል?+
11 እጅህን ይኸውም ቀኝ እጅህን የሰበሰብከው ለምንድን ነው?+
እጅህን ከጉያህ* አውጥተህ አጥፋቸው።
12 ይሁንና በምድር ላይ ታላቅ የማዳን ሥራ የሚፈጽመው አምላክከጥንት ጀምሮ ንጉሤ ነው።+
13 በብርታትህ ባሕሩን አናወጥክ፤+በውኃ ውስጥ ያሉትን ግዙፍ የባሕር ፍጥረታት ራስ ሰባበርክ።
14 የሌዋታንን* ራሶች አደቀቅክ፤በበረሃ ለሚኖሩት ሰዎች ምግብ አድርገህ ሰጠሃቸው።
15 ለምንጮችና ለጅረቶች መውጫ ያበጀኸው አንተ ነህ፤+ሳያቋርጡ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅክ።+
16 ቀኑ የአንተ ነው፤ ሌሊቱም የአንተ ነው።
ብርሃንንና ፀሐይን* ሠራህ።+
17 የምድርን ወሰኖች ሁሉ ደነገግክ፤+በጋና ክረምት እንዲፈራረቁ አደረግክ።+
18 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላት እንደተሳለቀ፣ሞኝ ሕዝብ ስምህን እንዴት እንዳቃለለ አስብ።+
19 የዋኖስህን ሕይወት* ለዱር አራዊት አትስጥ።
የተጎሳቆለውን ሕዝብህን ሕይወት ለዘላለም አትርሳ።
20 ቃል ኪዳንህን አስብ፤በምድሪቱ ላይ ያሉት ጨለማ ቦታዎች የዓመፅ መናኸሪያ ሆነዋልና።
21 የተደቆሰው ሰው አዝኖ አይመለስ፤+ችግረኛውና ድሃው ስምህን ያወድስ።+
22 አምላክ ሆይ፣ ተነስ፤ ደግሞም ለራስህ ተሟገት።
ሞኝ ሰው ቀኑን ሙሉ እንዴት እንደሚሳለቅብህ አስብ።+
23 ጠላቶችህ የሚሉትን አትርሳ።
አንተን የሚዳፈሩ ሰዎች የሚያሰሙት ሁካታ ያለማቋረጥ ወደ ላይ እየወጣ ነው።