መዝሙር 75:1-10

  • አምላክ በትክክል ይፈርዳል

    • ክፉዎች የይሖዋን ጽዋ ይጠጣሉ (8)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። “ጥፋት አታምጣ” በተባለው ቅኝት የሚዜም ማህሌት። የአሳፍ+ መዝሙር። 75  ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ አምላክ ሆይ፣ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ስምህ ከእኛ ጋር ነው፤+ሰዎችም ድንቅ ሥራዎችህን ያውጃሉ።   አንተ እንዲህ ትላለህ፦ “ጊዜ ስወስንበትክክል እፈርዳለሁ።   ምድርና በላይዋ የሚኖሩ ሁሉ ሲቀልጡ፣ምሰሶዎቿን አጽንቼ ያቆምኩት እኔ ነኝ።” (ሴላ)   ጉራቸውን ለሚነዙት “ጉራ አትንዙ” እላለሁ፤ ክፉዎቹንም እንዲህ እላለሁ፦ “ኃይላችሁን* ከፍ ከፍ አታድርጉ።   ኃይላችሁን* ወደ ላይ ከፍ አታድርጉ፤ወይም በትዕቢት አትናገሩ።   ክብር ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብወይም ከደቡብ አይመጣምና።   አምላክ ፈራጅ ነውና።+ አንዱን ያዋርዳል፤ ሌላውን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል።+   በይሖዋ እጅ ጽዋ አለና፤+የወይን ጠጁ አረፋ ያወጣል፤ ደግሞም ሙሉ በሙሉ የተደባለቀ ነው። እሱ በእርግጥ ያፈሰዋል፤በምድርም ላይ ያሉ ክፉዎች ሁሉ ከነአተላው ይጨልጡታል።”+   እኔ ግን ይህን ለዘላለም አውጃለሁ፤ለያዕቆብ አምላክ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። 10  እሱ እንዲህ ይላልና፦ “የክፉዎችን ኃይል* በሙሉ እቆርጣለሁ፤የጻድቅ ሰው ኃይል ግን ከፍ ከፍ ይላል።”

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ቀንዳችሁን።”
ቃል በቃል “ቀንዳችሁን።”
ቃል በቃል “ቀንድ።”