መዝሙር 77:1-20

  • በጭንቀት ጊዜ የቀረበ ጸሎት

    • በአምላክ ሥራዎች ላይ ማሰላሰል (11, 12)

    • “አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?” (13)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በየዱቱን።* የአሳፍ+ መዝሙር። ማህሌት። 77  ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ እሱም ይሰማኛል።+   በጭንቀት በተዋጥኩ ቀን ይሖዋን እፈልጋለሁ።+ በሌሊት እጆቼ ያለምንም ፋታ ወደ እሱ እንደተዘረጉ ናቸው፤ ልጽናና አልቻልኩም።*   አምላክን ሳስታውስ እቃትታለሁ፤+ተጨንቄአለሁ፤ ኃይሌም ከዳኝ።*+ (ሴላ)   የዓይኔ ቆብ እንዳይከደን ያዝከው፤በጣም ተረብሻለሁ፤ መናገርም አልችልም።   የድሮውን ጊዜ መለስ ብዬ አሰብኩ፤+የጥንቶቹን ዓመታት አስታወስኩ።   መዝሙሬን* በሌሊት አስታውሳለሁ፤+በልቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ፤+በጥሞና እመረምራለሁ።*   ይሖዋ ለዘላለም ይጥለናል?+ ዳግመኛስ ሞገስ አያሳየንም?+   ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ተቋርጧል? የተስፋ ቃሉስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ከንቱ ሆኖ ይቀራል?   አምላክ ሞገሱን ማሳየት ረስቷል?+ወይስ ቁጣው ምሕረት ከማሳየት እንዲቆጠብ አድርጎታል? (ሴላ) 10  “እኔን የሚያስጨንቀኝ* ይህ ነው፦+ ልዑሉ አምላክ ለእኛ ያለውን አመለካከት* ለውጧል” እያልኩ ልኖር ነው? 11  ያህ ያከናወናቸውን ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ጥንት የፈጸምካቸውን ድንቅ ተግባሮች አስታውሳለሁ። 12  በሥራዎችህም ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤ያከናወንካቸውንም ነገሮች አውጠነጥናለሁ።+ 13  አምላክ ሆይ፣ መንገዶችህ ቅዱስ ናቸው። አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?+ 14  አንተ ድንቅ ነገሮችን የምታከናውን እውነተኛ አምላክ ነህ።+ ብርታትህን ለሕዝቦች ገልጠሃል።+ 15  በኃይልህ* ሕዝብህን ይኸውምየያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች ታድገሃል።*+ (ሴላ) 16  አምላክ ሆይ፣ ውኃዎቹ አዩህ፤ውኃዎቹ ሲያዩህ ተረበሹ።+ ጥልቅ ውኃዎቹም ተናወጡ። 17  ደመናት ውኃ አዘነቡ። በደመና የተሸፈኑት ሰማያት አንጎደጎዱ፤ፍላጻዎችህም እዚህም እዚያም ተወነጨፉ።+ 18  የነጎድጓድህ ድምፅ+ እንደ ሠረገላ ድምፅ ነበር፤የመብረቅ ብልጭታዎች በዓለም* ላይ አበሩ፤+ምድር ተናወጠች፤ ደግሞም ተንቀጠቀጠች።+ 19  መንገድህ በባሕር ውስጥ ነበር፤+ጎዳናህም በብዙ ውኃዎች ውስጥ ነበር፤ይሁንና የእግርህ ዱካ ሊገኝ አልቻለም። 20  ሕዝብህን በሙሴና በአሮን እጅ+እንደ መንጋ መራህ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ነፍሴ ልትጽናና አልቻለችም።”
ቃል በቃል “መንፈሴም ዛለ።”
ወይም “በባለ አውታር መሣሪያ የምጫወተውን ሙዚቃ።”
ቃል በቃል “መንፈሴ በጥሞና ይመረምራል።”
ቃል በቃል “ቀኝ እጁን።”
ወይም “የሚያቆስለኝ።”
ቃል በቃል “በክንድህ።”
ቃል በቃል “ዋጅተሃል።”
ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”