መዝሙር 78:1-72

  • የአምላክ እንክብካቤና የእስራኤላውያን እምነት ማጣት

    • ለመጪው ትውልድ ተናገሩ (2-8)

    • “በአምላክ ላይ እምነት አልጣሉም” (22)

    • ‘የሰማይ እህል’ (24)

    • ‘የእስራኤልን ቅዱስ እጅግ አሳዘኑት’ (41)

    • ከግብፅ አንስቶ እስከ ተስፋይቱ ምድር (43-55)

    • ‘አምላክን ተገዳደሩት’ (56)

ማስኪል።* የአሳፍ+ መዝሙር። 78  ሕዝቤ ሆይ፣ ሕጌን* አዳምጥ፤ከአፌ ወደሚወጣው ቃል ጆሮህን አዘንብል።   አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ። በጥንት ዘመን የተነገሩትን እንቆቅልሾች አቀርባለሁ።+   የሰማናቸውንና ያወቅናቸውን ነገሮች፣አባቶቻችን ለእኛ የተረኩልንን፣+   ከልጆቻቸው አንደብቀውም፤ይሖዋ ያከናወናቸውን የሚያስመሰግኑ ሥራዎችና ብርታቱን፣+ደግሞም የሠራቸውን አስደናቂ ነገሮች+ለመጪው ትውልድ እንተርካለን።+   እሱ ለያዕቆብ ማሳሰቢያ ሰጠ፤በእስራኤልም ሕግ ደነገገ፤እነዚህን ነገሮች ለልጆቻቸው እንዲያሳውቁአባቶቻችንን አዘዛቸው፤+   ይህም ቀጣዩ ትውልድ፣ገና የሚወለዱት ልጆች እነዚህን ነገሮች እንዲያውቁ ነው።+ እነሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ይተርካሉ።+   በዚህ ጊዜ እነሱ ትምክህታቸውን በአምላክ ላይ ይጥላሉ። የአምላክን ሥራዎች አይረሱም፤+ይልቁንም ትእዛዛቱን ይጠብቃሉ።+   ያን ጊዜ እንደ አባቶቻቸውእልኸኛና ዓመፀኛ ትውልድ፣+ደግሞም ልቡ የሚወላውልና*+መንፈሱ ለአምላክ ታማኝ ያልሆነ ትውልድ አይሆኑም።   ኤፍሬማውያን ቀስት የታጠቁ ነበሩ፤ይሁንና በጦርነት ቀን ወደ ኋላ አፈገፈጉ። 10  የአምላክን ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤+በሕጉም ለመመላለስ ፈቃደኛ አልሆኑም።+ 11  በተጨማሪም ያደረጋቸውን ነገሮች፣ያሳያቸውን ድንቅ ሥራዎች ረሱ።+ 12  በአባቶቻቸው ፊት በግብፅ አገር፣በጾዓን+ ምድር አስደናቂ ነገሮች አከናውኖ ነበር።+ 13  በዚያ አቋርጠው እንዲሄዱ ባሕሩን ከፈለው፤ውኃዎቹንም እንደ ግድብ አቆመ።*+ 14  ቀን በደመና፣ ሌሊቱን ሙሉ ደግሞበእሳት ብርሃን መራቸው።+ 15  በምድረ በዳ ዓለቶችን ሰነጠቀ፤ከጥልቅ ውኃ የሚጠጡ ያህል እስኪረኩ ድረስ አጠጣቸው።+ 16  ከቋጥኝ ውስጥ ወራጅ ውኃ አወጣ፤ውኃዎችም እንደ ወንዝ እንዲፈስሱ አደረገ።+ 17  እነሱ ግን በበረሃ፣ በልዑሉ አምላክ ላይ በማመፅበእሱ ላይ ኃጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ፤+ 18  እንዲሁም የተመኙትን* ምግብ እንዲሰጣቸው በመጠየቅአምላክን በልባቸው ተገዳደሩት።*+ 19  “አምላክ በምድረ በዳ ማዕድ ማዘጋጀት ይችላል?” በማለትበአምላክ ላይ አጉረመረሙ።+ 20  እነሆ፣ ውኃ እንዲፈስና ጅረቶች እንዲንዶለዶሉዓለትን መታ።+ ይሁንና “ዳቦስ ሊሰጠን ይችላል?ወይስ ለሕዝቡ ሥጋ ሊያቀርብ ይችላል?” አሉ።+ 21  ይሖዋ በሰማቸው ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤+በያዕቆብ ላይ እሳት+ ተቀጣጠለ፤በእስራኤልም ላይ ቁጣው ነደደ፤+ 22  ምክንያቱም በአምላክ ላይ እምነት አልጣሉም፤+እነሱን የማዳን ችሎታ እንዳለው አላመኑም። 23  ስለዚህ በላይ ያሉትን በደመና የተሸፈኑ ሰማያት አዘዘ፤የሰማይንም በሮች ከፈተ። 24  የሚበሉት መና አዘነበላቸው፤የሰማይንም እህል ሰጣቸው።+ 25  ሰዎች የኃያላንን*+ ምግብ በሉ፤እስኪጠግቡ ድረስ እንዲበሉ በቂ ምግብ አቀረበላቸው።+ 26  የምሥራቁን ነፋስ በሰማይ አስነሳ፤በኃይሉም የደቡብ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ።+ 27  ሥጋንም እንደ አፈር፣ወፎችንም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አዘነበላቸው። 28  በሰፈሩ መካከል፣በድንኳኖቹም ሁሉ ዙሪያ እንዲወድቁ አደረገ። 29  እነሱም በሉ፤ ከልክ በላይም ጠገቡ፤የተመኙትን ነገር ሰጣቸው።+ 30  ሆኖም ምኞታቸውን ሙሉ በሙሉ ከማርካታቸው በፊት፣ምግባቸው ገና በአፋቸው ውስጥ እያለ 31  የአምላክ ቁጣ በእነሱ ላይ ነደደ።+ ኃያላን ሰዎቻቸውን ገደለ፤+የእስራኤልን ወጣቶች ጣለ። 32  ይህም ሆኖ በኃጢአታቸው ገፉበት፤+አስደናቂ በሆኑ ሥራዎቹም አላመኑም።+ 33  ስለዚህ ዘመናቸው እንደ እስትንፋስ እንዲያበቃ፣+ዕድሜያቸውም በድንገተኛ ሽብር እንዲያከትም አደረገ። 34  ሆኖም በገደላቸው ቁጥር እሱን ይሹ ነበር፤+ተመልሰው አምላክን ይፈልጉ ነበር፤ 35  ይህን የሚያደርጉት አምላክ ዓለታቸው እንደሆነ፣+ልዑሉ አምላክም እንደሚዋጃቸው* በማስታወስ ነበር።+ 36  እነሱ ግን በአፋቸው ሊያታልሉት ሞከሩ፤በምላሳቸውም ዋሹት። 37  ልባቸው ለእሱ የጸና አልነበረም፤+ለቃል ኪዳኑም ታማኞች አልነበሩም።+ 38  እሱ ግን መሐሪ ነው፤+በደላቸውን ይቅር ይል* ነበር፤ ደግሞም አላጠፋቸውም።+ ቁጣውን ሁሉ ከመቀስቀስ ይልቅብዙ ጊዜ ስሜቱን ይገታ ነበር።+ 39  ነፍሶ ዳግመኛ የማይመለስ ነፋስ፣*ሥጋ መሆናቸውንም አስታውሷልና።+ 40  በምድረ በዳ ስንት ጊዜ በእሱ ላይ ዓመፁ!+በበረሃ ሳሉም ብዙ ጊዜ ስሜቱን ጎዱት!+ 41  ደግመው ደጋግመው አምላክን ተፈታተኑት፤+የእስራኤልንም ቅዱስ እጅግ አሳዘኑት።* 42  እነሱን ከጠላት የታደገበትን* ቀን፣ኃይሉንም* አላስታወሱም፤+ 43  በግብፅ አስደናቂ ምልክቶችን፣በጾዓን ምድርም ተአምራቱን እንዴት እንዳሳየ አላሰቡም፤+ 44  እንዲሁም ከጅረቶቻቸው መጠጣት እንዳይችሉየአባይን የመስኖ ቦዮች እንዴት ወደ ደም እንደለወጠ ዘነጉ።+ 45  ይበሏቸው ዘንድ የተናካሽ ዝንቦችን መንጋ ሰደደባቸው፤+ያጠፏቸውም ዘንድ እንቁራሪቶችን ላከባቸው።+ 46  ሰብላቸውን ለማይጠግብ አንበጣ፣የድካማቸውን ፍሬ ለአንበጣ መንጋ ሰጠ።+ 47  የወይን ተክላቸውን በበረዶ፣የሾላ ዛፎቻቸውንም በበረዶ ድንጋይ አጠፋ።+ 48  የጋማ ከብቶቻቸውን ለበረዶ፣+መንጎቻቸውንም ለመብረቅ ብልጭታ* ዳረገ። 49  የሚነድ ቁጣውን፣ንዴቱን፣ መዓቱንና መቅሰፍቱንእንዲሁም ጥፋት የሚያመጡ የመላእክት ሠራዊትን ላከባቸው። 50  ለቁጣው መንገድ ጠረገ። ከሞት አላተረፋቸውም፤*ለቸነፈርም አሳልፎ ሰጣቸው። 51  በመጨረሻም የግብፅን በኩሮች በሙሉ፣በካም ድንኳኖች ውስጥ ከሚገኙትም መካከል የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ።+ 52  ከዚያም ሕዝቡን እንደ በጎች እንዲወጡ አደረገ፤በምድረ በዳም እንደ መንጋ መራቸው።+ 53   በአስተማማኝ ሁኔታ መራቸው፤አንዳች ፍርሃትም አልተሰማቸውም፤+ባሕሩም ጠላቶቻቸውን ዋጠ።+ 54  ደግሞም ቅዱስ ወደሆነው ምድሩ፣ቀኝ እጁ የራሱ ወዳደረገው ወደዚህ ተራራማ ክልል አመጣቸው።+ 55  ብሔራቱን ከፊታቸው አባረረ፤+በመለኪያ ገመድም ርስት አከፋፈላቸው፤+የእስራኤልን ነገዶች በቤቶቻቸው እንዲኖሩ አደረገ።+ 56  እነሱ ግን ልዑሉን አምላክ ተገዳደሩት፤* በእሱም ላይ ዓመፁ፤+ማሳሰቢያዎቹን ችላ አሉ።+ 57  በተጨማሪም ጀርባቸውን ሰጡ፤ እንደ አባቶቻቸውም ከሃዲዎች ሆኑ።+ ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ነበሩ።+ 58  ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎቻቸው ብዙ ጊዜ አሳዘኑት፤+በተቀረጹ ምስሎቻቸውም ለቁጣ* አነሳሱት።+ 59  አምላክ ሰምቶ በጣም ተቆጣ፤+በመሆኑም እስራኤልን እርግፍ አድርጎ ተወው። 60  በመጨረሻም በሴሎ የሚገኘውን የማደሪያ ድንኳን፣በሰው ልጆች መካከል ይኖርበት የነበረውን ድንኳን ተወው።+ 61  የብርታቱ ምልክት ተማርኮ እንዲወሰድ ፈቀደ፤ግርማ ሞገሱን በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ።+ 62  ሕዝቡን ለሰይፍ አሳልፎ ሰጠ፤+በርስቱም ላይ እጅግ ተቆጣ። 63  ወጣቶቹን እሳት በላቸው፤ለድንግሎቹም የሠርግ ዘፈን አልተዘፈነላቸውም።* 64  ካህናቱ በሰይፍ ወደቁ፤+የገዛ መበለቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም።+ 65  ከዚያም ይሖዋ፣ የወይን ጠጅ ስካሩ እንደለቀቀው ኃያል ሰውከእንቅልፍ እንደነቃ ሆኖ ተነሳ።+ 66  ጠላቶቹንም አሳዶ ወደ ኋላ መለሳቸው፤+ለዘለቄታው ውርደት አከናነባቸው። 67  የዮሴፍን ድንኳን ናቀ፤የኤፍሬምን ነገድ አልመረጠም። 68  ከዚህ ይልቅ የይሁዳን ነገድ፣የሚወደውን የጽዮንን ተራራ+ መረጠ።+ 69  መቅደሱን እንደ ሰማያት ጽኑ አድርጎ ሠራው፤*+ለዘላለምም እንደመሠረታት ምድር አድርጎ ገነባው።+ 70  አገልጋዩን ዳዊትን መረጠ፤+ከበጎች ጉረኖ ወስዶ፣+ 71  የሚያጠቡ በጎችን ከመጠበቅም አንስቶበሕዝቡ በያዕቆብ፣ በርስቱም በእስራኤል ላይእረኛ እንዲሆን ሾመው።+ 72  እሱም በንጹሕ ልብ* ጠበቃቸው፤+በተካኑ እጆቹም መራቸው።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “መመሪያዬን፤ ትምህርቴን።”
ቃል በቃል “ልቡን ያላዘጋጀና።”
ወይም “እንደ ግድግዳ አቆመ።”
ወይም “ነፍሳቸው የተመኘችውን።”
ቃል በቃል “ፈተኑት።”
ወይም “የመላእክትን።”
ወይም “እንደሚበቀልላቸው።”
ቃል በቃል “ይሸፍን።”
“መንፈስ እንደሚወጣና እንደማይመለስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “አበሳጩት።”
ቃል በቃል “የዋጀበትን።”
ቃል በቃል “እጁንም።”
“ለኃይለኛ ትኩሳት” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ነፍሳቸውን ከሞት አላተረፈም።”
ቃል በቃል “ፈተኑት።”
ወይም “ለቅናት።”
ቃል በቃል “የእሱ ድንግሎች አልተወደሱም።”
ቃል በቃል “መቅደሱን እንደ አርያም ገነባ።”
መዝ 7:8 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።