መዝሙር 79:1-13
የአሳፍ+ ማህሌት።
79 አምላክ ሆይ፣ ብሔራት ርስትህን+ ወረውታል፤ቅዱስ መቅደስህንም አርክሰዋል፤+ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር አድርገዋታል።+
2 የአገልጋዮችህን ሬሳ ለሰማይ ወፎች፣የታማኝ አገልጋዮችህንም ሥጋ ለምድር አራዊት ምግብ አድርገው ሰጥተዋል።+
3 ደማቸውን በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፤እነሱንም የሚቀብር አንድም ሰው አልተረፈም።+
4 በጎረቤቶቻችን ዘንድ መሳለቂያ ሆንን፤+በዙሪያችን ያሉትም ያፌዙብናል፤ ደግሞም ይዘብቱብናል።
5 ይሖዋ ሆይ፣ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?+
ቁጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?+
6 አንተን በማያውቁ ብሔራት፣ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ ቁጣህን አፍስስ።+
7 ያዕቆብን በልተውታልና፤የትውልድ አገሩንም አውድመዋል።+
8 አባቶቻችን በሠሩት ስህተት እኛን ተጠያቂ አታድርገን።+
ፈጥነህ ምሕረት አድርግልን፤+በጭንቀት ተውጠናልና።
9 አዳኛችን የሆንክ አምላክ ሆይ፣ለታላቁ ስምህ ስትል እርዳን፤+ለስምህም ስትል ታደገን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በለን።*+
10 ብሔራት “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ?+
በፈሰሰው የአገልጋዮችህ ደም የተነሳ የሚወሰድባቸውን የበቀል እርምጃ፣ዓይናችን እያየ ብሔራት ይወቁት።+
11 እስረኛው የሚያሰማውን ሲቃ ስማ።+
ሞት የተፈረደባቸውን* በታላቅ ኃይልህ* አድናቸው።*+
12 ይሖዋ ሆይ፣ ጎረቤቶቻችን በአንተ ላይ በመሳለቃቸው+ሰባት እጥፍ አድርገህ ብድራታቸውን ክፈላቸው።+
13 በዚህ ጊዜ እኛ ሕዝቦችህ፣ በመስክህ ያሰማራኸን መንጋ፣+ለዘላለም ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ከትውልድ እስከ ትውልድም ውዳሴህን እናሰማለን።+