መዝሙር 80:1-19

  • የእስራኤል እረኛ ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንዲመልሳቸው የቀረበ ልመና

    • “አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን” (3)

    • የአምላክ የወይን ተክል የሆነው እስራኤል (8-15)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ “በአበቦች” የሚዘመር። ማስታወሻ። የአሳፍ+ መዝሙር። ማህሌት። 80  ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራየእስራኤል እረኛ ሆይ፣+ አዳምጥ። ከኪሩቤል በላይ* በዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣+ብርሃን አብራ።*   በኤፍሬም፣ በቢንያምና በምናሴ ፊትኃያልነትህን አሳይ፤+መጥተህም አድነን።+   አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤+እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+   የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝቦችህ የሚያቀርቡትን ጸሎት የምትጠላው* እስከ መቼ ነው?+   እንባን እንደ ምግብ ትመግባቸዋለህ፤ደግሞም እንባ ትግታቸዋለህ።   ለጎረቤቶቻችን የጠብ ምክንያት አደረግከን፤ጠላቶቻችን እንዳሻቸው ያላግጡብናል።+   የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+   የወይን ተክል+ ከግብፅ እንድትወጣ አደረግክ። ብሔራትን አባረህ እሷን ተከልክ።+   መሬቱን መነጠርክላት፤እሷም ሥር ሰዳ በምድሪቱ ላይ ተንሰራፋች።+ 10  ተራሮች በጥላዋ፣የአምላክ አርዘ ሊባኖሶችም በቅርንጫፎቿ ተሸፈኑ። 11  ቅርንጫፎቿ እስከ ባሕሩ፣ቀንበጦቿም እስከ ወንዙ* ድረስ ተዘረጉ።+ 12  በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ፍሬዋን እንዲቀጥፉ፣+የወይን እርሻዋን የድንጋይ ቅጥሮች ያፈረስከው ለምንድን ነው?+ 13  ከጫካ የወጡ የዱር አሳማዎች ያወድሟታል፤በሜዳ ያሉ የዱር አራዊትም ይበሏታል።+ 14  የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ እባክህ ተመለስ። ከሰማይ ወደ ታች እይ፤ ተመልከትም! ይህችን የወይን ተክል ተንከባከባት፤+ 15  ቀኝ እጅህ የተከላትን ግንድ*+ በእንክብካቤ ያዛት፤ለራስህ ስትል ያጠነከርከውንም ልጅ* ተመልከት።+ 16  እሷ ተቆርጣ በእሳት ተቃጥላለች።+ ሕዝቡ ከተግሣጽህ* የተነሳ ይጠፋል። 17  እጅህ በቀኝህ ላለው ሰው፣ለራስህም ስትል ብርቱ ላደረግከው የሰው ልጅ ድጋፍ ትስጥ።+ 18  እኛም ከአንተ አንርቅም። ስምህን መጥራት እንድንችል በሕይወት አኑረን። 19  የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ቀድሞው ሁኔታችን መልሰን፤እንድንም ዘንድ ፊትህን በእኛ ላይ አብራ።+

የግርጌ ማስታወሻ

“በኪሩቤል መካከል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ብርሃንህን ግለጥ።”
ቃል በቃል “በሚያቀርቡት ጸሎት ቁጣህ የሚነደው።”
የኤፍራጥስን ወንዝ ያመለክታል።
ወይም “የወይን ተክል ዋና ግንድ።”
ወይም “ቅርንጫፍ።”
ቃል በቃል “ከፊትህ ተግሣጽ።”