መዝሙር 81:1-16

  • ታዛዥ እንዲሆኑ የቀረበ ማሳሰቢያ

    • ባዕዳን አማልክትን አታምልክ (9)

    • ‘ምነው ባዳመጥከኝ ኖሮ!’ (13)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በጊቲት።* የአሳፍ+ መዝሙር። 81  ብርታታችን ለሆነው አምላክ+ እልል በሉ። ለያዕቆብ አምላክ በድል አድራጊነት ስሜት ጩኹ።   ሙዚቃውን መጫወት ጀምሩ፤ አታሞም ምቱ፤ደስ የሚያሰኘውን በገና ከባለ አውታር መሣሪያ ጋር ተጫወቱ።   አዲስ ጨረቃ በምትታይበት፣ሙሉ ጨረቃም ወጥታ በዓል በምናከብርበት ዕለት+ ቀንደ መለከት ንፉ።+   ይህ ለእስራኤል የተሰጠ ድንጋጌ፣የያዕቆብም አምላክ ያስተላለፈው ውሳኔ ነውና።+   በግብፅ ምድር ላይ ባለፈ ጊዜ፣+ይህን ለዮሴፍ ማሳሰቢያ አድርጎ ሰጠው።+ እኔም የማላውቀውን ድምፅ* ሰማሁ፦   “ሸክሙን ከትከሻው ላይ አነሳሁለት፤+እጆቹ ቅርጫት ከመያዝ አረፉ።   በጨነቀህ ጊዜ ጠራኸኝ፤ እኔም ታደግኩህ፤+ከነጎድጓዳማው ደመና* መለስኩልህ።+ የመሪባ* ውኃዎች ባሉበት ስፍራ ፈተንኩህ።+ (ሴላ)   ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔም እመሠክርብሃለሁ። እስራኤል ሆይ፣ ምነው ብታዳምጠኝ!+   በመካከልህ እንግዳ አምላክ አይኖርም፤ለባዕድ አምላክም አትሰግድም።+ 10  ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።+ አፍህን በሰፊው ክፈት፤ እኔም በምግብ እሞላዋለሁ።+ 11  ሕዝቤ ግን ድምፄን አልሰማም፤እስራኤል ለእኔ አይገዛም።+ 12  በመሆኑም እልኸኛ ልባቸውን እንዲከተሉ ተውኳቸው፤ትክክል መስሎ የታያቸውን አደረጉ።*+ 13  ምነው ሕዝቤ ቢያዳምጠኝ ኖሮ!+ምነው እስራኤል በመንገዴ ቢመላለስ ኖሮ!+ 14  ጠላቶቻቸውን ወዲያውኑ ባንበረከክኋቸው፣እጄን በባላጋራዎቻቸው ላይ በሰነዘርኩ ነበር።+ 15  ይሖዋን የሚጠሉ በፊቱ ይሸማቀቃሉ፤የሚደርስባቸውም ነገር* ዘላለማዊ ነው። 16  እሱ ግን ምርጡን ስንዴ* ይመግባችኋል፤*+ከዓለት በሚገኝ ማርም ያጠግባችኋል።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ቋንቋ።”
“ጠብ” የሚል ትርጉም አለው።
ቃል በቃል “በነጎድጓድ መሰወሪያ ቦታ።”
ቃል በቃል “በምክራቸው ተመላለሱ።”
ቃል በቃል “ዘመናቸውም።”
ቃል በቃል “የስንዴ ስብ።”
ቃል በቃል “ይመግበዋል።” የአምላክን ሕዝብ ያመለክታል።