መዝሙር 85:1-13

  • ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንዲመልሳቸው የቀረበ ጸሎት

    • አምላክ ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራል (8)

    • “ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ይገናኛሉ” (10)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት። 85  ይሖዋ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳይተሃል፤+የተማረኩትን የያዕቆብ ልጆች መልሰሃል።+   የሕዝብህን በደል ተውክ፤ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ።*+ (ሴላ)   ንዴትህን ሁሉ ገታህ፤ከብርቱ ቁጣህም ተመለስክ።+   የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞ ሁኔታችን መልሰን፤*በእኛ የተነሳ ያደረብህን ቁጣም መልስ።+   በእኛ ላይ የምትቆጣው ለዘላለም ነው?+ ቁጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይዘልቃል?   ሕዝቦችህ በአንተ ሐሴት እንዲያደርጉ፣ዳግመኛ እንድናንሰራራ አታደርገንም?+   ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህን አሳየን፤+ማዳንህንም ለግሰን።   እውነተኛው አምላክ ይሖዋ የሚናገረውን እሰማለሁ፤እሱ ለሕዝቡና ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራልና፤+ብቻ እንደቀድሞው በራሳቸው ከልክ በላይ አይተማመኑ።+   ክብሩ በምድራችን እንዲኖር፣እሱን ለሚፈሩት ማዳኑ በእርግጥ ቅርብ ነው።+ 10  ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ይገናኛሉ፤ጽድቅና ሰላም ይሳሳማሉ።+ 11  ታማኝነት ከምድር ትበቅላለች፤ጽድቅም ከሰማያት ወደ ታች ይመለከታል።+ 12  አዎ፣ ይሖዋ መልካም ነገር* ይሰጣል፤+ምድራችንም ምርቷን ትሰጣለች።+ 13  ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤+ለእርምጃውም መንገድ ያዘጋጃል።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ሸፈንክ።”
ወይም “መልሰህ ሰብስበን።”
ወይም “ብልጽግና።”