መዝሙር 87:1-7

  • ጽዮን፣ የእውነተኛው አምላክ ከተማ

    • በጽዮን የተወለዱ (4-6)

የቆሬ ልጆች+ መዝሙር። ማህሌት። 87  የአምላክ ከተማ የተመሠረተችው በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው።+   ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ሁሉ ይበልጥየጽዮንን በሮች ይወዳል።+   የእውነተኛው አምላክ ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች እየተነገሩ ነው።+ (ሴላ)   እኔን ከሚያውቁኝ* መካከል ረዓብንና*+ ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ኢትዮጵያን* ጨምሮ ፍልስጤምና ጢሮስም ይገኙበታል። እንዲህም ይባላል፦ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው።”   ስለ ጽዮን ደግሞ እንዲህ ይባላል፦ “ይሄኛውም ሆነ ያኛው የተወለደው በእሷ ውስጥ ነው።” ልዑሉ አምላክም አጽንቶ ይመሠርታታል።   ይሖዋ ሕዝቡን ሲመዘግብ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው” ብሎ ያስታውቃል። (ሴላ)   ዘማሪዎችና+ ጨፋሪዎች*+ “ምንጮቼ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛሉ”*+ ይላሉ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ለእኔ እውቅና ከሚሰጡት።”
ይህ ቃል ግብፅን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል።
ወይም “ኩሽን።”
ወይም “ክብ ሠርተው የሚጨፍሩ።”
ወይም “ለእኔ የሁሉ ነገር ምንጭ አንቺ ነሽ።”